የፖለቲካ ፓርቲዎች ግኑኝነት መጠናከር የፖለቲካ ልምምድ መሻሻል ውጤት ነው፦ አቶ ሰለሞን አየለ

Spread the love

የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስበርስ ግኑኝነት መጠናከር የፖለቲካ ልምምድ መሻሻል ውጤት መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢና የካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አየለ ገለጹ።

በክልሉ ህጋዊ ፍቃድ አግኝተው የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ጥምረት ምክር ቤት አባላት በካፋ ዞን ሸሾንዴ ወረዳ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ እየጎበኙ ይገኛል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች እርስበርስ ግኑኝነት መጠናከር የፖለቲካ ልምምድ መሻሻል ውጤት መሆኑን የገለጹት የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን አየለ የጋራ ምክር ቤቱ በክልሉ ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ዙርያ ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተው እየሰራ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ከቀደመው የመቃቃርና የጠላትነት ፍረጃ በመውጣት ለሀገር ዕድገትና ለህዝብ ጥቅም በጋራ መስራት መጀመራቸው ተራማጅ አስተሳሰብ ላይ ማንገባቸውን ማሳያ መሆኑን የገለጹት አቶ ሰለሞን ጉብኝቱ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ጠንካራ ተግባራትን ለማስቀጠልና በድክመት የታዩትን ጉዳዮች በጋራ በመታገል ለማረም ዓላማ ያደረገ መሆኑን ግልጸዋል።

የክልሉን የልማት ፀጋዎች ወደ ሀብት ቀይሮ የህዝቡን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ሁሉም ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰላም አምባሳደርነት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ያስገነዘቡት አቶ ሰለሞ ቀጣይነት ባለው መልኩ ፓርቲዎች መተጋገዝና መተባበር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የትብብርና ምክክር ባህልን ማዳበር የሰለጠነ የፖለቲካ ትግል መሆኑን የገለጹት የካፋ ዞን ረዳት የመንግሥት ተጠሪ ወ/ሮ ጽዮን ታዬ በበኩላቸው በዞኑ ከሚንቀሳቀሱ በቁጥር 8 ከሚኾኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሁሉም መስክ የተጠናከረ ግኑኝነት መኖሩን ነው ያስረዱት።

በገዢው ፓርቲ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች መሠረት የህዝብ ኑሮ ለማሻሻልና የመልካም ጥያቄዎች ለመፍታት በዞኑ እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴም ረዳት የመንግሥት ተጠሪዋ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የጥምረቱ አባላት በዞኑ ሺሾንዴ ወረዳ በወጣቶች፣ በማህበራትና በአስርሶአደሮች እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የሌማት ትሩፋት እንቅስቃሴዎች ተዘዋውሮ እየጎበኙ ይገኛል።

በጉብኝት የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስራ-አስፈጻሚዎችና አመራሮች እንዲሁም የካፋ ዞንና የሽሾንዴ ወረዳ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *