በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአስተዳደር ብልጽግና ህብረት የ2017 ዓ/ም ዕቅድ አፈጻጸምና የ2018 ዓ/ም ዕቅድ ዙሪያ ከአባላት ጋር እየገመገመ ነው።

Spread the love

በበጀት ዓመቱ ታቅደው በብልጽግና ቤተሰብ ደረጃ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት ህብረቱ ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ አቅርበዋል ።

የህብረቱ ሰብሳቢ ባቀረቡት ሪፖርት የብልጽግና ቤተሰብ በበጀት ዓመቱ ዕቅዳቸውን ውጤታማ እንዲያደርጉ ተገቢው የድጋፍና ክትትል ስራዎች መሰራታቸውን አብራርተዋል ።

ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚወርዱ ሀገር አቀፍና ክልል አቀፍ ይዘት ያሏቸውን ተልዕኮ ለመፈጸም እንዲያስችል የአባላት አቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መሰራታቸውን አብራርተዋል ።

በህብረቱ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና በአፈጻጸም ሂደት የነበሩ ጉድለቶችን እንዲሁም የ2018 ዓ/ም ጠቋሚ ዕቅድ ቀርቦ አባላት መክረውበታል።

አባላት በበጀት ዓመቱ የተገኘውን ውጤት በማስቀጠል የታዩ ደካማ አፈጻጸሞችን በመለየት በቀጣይ በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ መስራት አለብን ብለዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *