የታክስ ስወራና ማጭበርበር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ የክልሉን የገቢ አሰባሰብ አቅም ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ እና የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር በጋራ በመሆን በታክስ ህግ ተገዢነት ዙሪያ ከዞን ገቢዎች መምሪያ ፣ከ6ቱ የዞን ማዕከል ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ የግብር ህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት በላይ፣በአሁኑ ጊዜ የታክስ አስተዳደር ስርዓት እየዘመነ መምጣቱን ገልፀው የግብር ህግ ተገዥነትን በጋራ ማሳደግ እንደሚገባም ተጠቅሰዋል።

የታክስ ስወራና ማጭበርበር ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ የክልሉን የገቢ አቅምን ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፀደቀ ከፍታው ባስተላለፉት መልዕክት፣የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የገቢ አሰባሰብ አቅም ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የታክስ አሰባሰብ ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት የግንዛቤ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው የታክስ ህግ ማስከበር ላይም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እንቅስቃሴ መጀመሩን አስረድተዋል።

በመድረኩ የ2017 ዓ.ም በህግ ተገዥነት ዙሪያ የተሰሩ አፈጻጸም ሪፖርት የቢሮ ምክትልና የህግ ማስከበር ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ ትዕግስት በላይ እየቀረበ ይገኛል።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *