“ማሽቃሮ” የካፋ ህዝብ ማህበራዊ መስተጋብር የሚንፀባረቅበት ታላቅ በዓል ስለሆነ እንደ አባቶቻችን ተንከባክበን እናቆየዋለን:- የበዓሉ ተሳታፊ ወጣቶች

Spread the love

የካፈቾ ብሔር ዘመን መለወጫ “ማሽቃሮ” በተለያዩ ትይንቶች በቦንግ ሻምበቶ ተከብሯል።

በዓሉን ሲያከብሩ የነበሩት ወጣቶች ማሽቃሮ አዝመራው አልቆ አዲስ ብርሃን ጮራ የሚናይበት ተናፋቂ በዓል ነው ብለዋል።

ማሽቃሮ በካፈቾ ዘንድ ልዩ ስፍራ ያለውና በጉጉት የሚጠበቅ ዓመታዊ ትይንት በዓል ነው ያለው ወጣት ሙሉቀን ካሳሁን ይህ ዕሴት በቀላሉ እዚህ አልደረሰምና እኛም በባለቤትነት ስሜት የሚንኮራበትን ባህል በመለማመድ ለትውልድ እናሸጋግራለን ብለዋል።

ወጣት ነጃት ሠለሞን በበኩሏ ማሽቃሮ ዘር፣ ፆታ፣ እድሜ እና ሀይማኖት ሳንለያይ በአንድነት የሚናከብረው የጋራ ዕሴታችን ስለሆነ በዚህ ደረጃ ቀጥሎ ሊከበር እንደሚገባ ገልፀዋለች።

ወጣት መሳይ ኬሮ እና ወጣት ባንችአየሁ ክፍሌ በበኩላቸው ማሽቃሮ ተናፋቂና ካፋ የሚታወቅበት የጨዋታ፣ የአመጋገብ እንዲሁም ወጣቶችን ጨምሮ ሁሉም አጊጠው የሚወጡበት የአደባባይ በዓል ስለሆነ ልዩ ደስታ እንደፈጠረላቸው ጠቁመዋል።

ወጣት ማስረሻ ለገሠ በበኩሉ የካፋ ተወላጅ የሆንን ሁላችንም ከአባቶቻችን የተረከብነውን ይህን ድንቅ ኹነት ተንከባክበን ሊናቆየው ይገባል ብለዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ ጨምረው ማሽቃሮን እና ሌሎች ዕሴቶቻችንን ወጣቶችና ባለድርሻ አካላት በማጥናት፣ በመሰነድ እንዲሁም ዘመኑ በሚፈልገው ዘዴዎች ተጠቅመው እንዲያለሙ ብሎም ማንነታቸውን በአደባባይ እንዲያስተዋውቁ እና በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፏል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *