በህገ ወጥ መንገድ በባጃጅ ሲዘዋወር የነበረ ቤንዚን መያዙን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ

Spread the love

የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ተስፋዬ አበበ ለክልሉ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮምንኬሽን እንደገለፁት በቦንጋ ከተማ ዩንቨርስቲ ቀጠና ቦንጋ ግብርና ምርምር አከባቢ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሸ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-01986 ደም ባለሶስት እግር ባጃጅ ከጎጀብ ወደ ቦንጋ ከተማ ለማስገባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ከተያዘው ቤንዚን ውስጥ 12 ጀሪካን እና 35 ባለሁለት ሊትር ሃይላንድ በአጠቃላይ 310 ሊትር ቤንዝል መያዙን የገለፁት አዛዡ የባጃጅ አሽከርካሪው ተሽከርካሪውን ተሸከርካሪውን ጥሎ በመሰወሩ ፖሊስ ግለሰቡን ለመያዝ በክትትል ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በቦንጋ ከተማ የህገ ወጥ ነዳጅ ግብይት መኖሩን በአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታ መፍጠሩን ኢንስፔክተር ተስፋዬ አመልክተው በህገ ወጥ መንገድ ቤንዝል ሽያጭ የሚያከናውኑ አካላት መለየታቸውን ገልፀው በቀጣይ ፖሊስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

በመንግስት በከፍተኛ ድጎማ ወደሀገር የሚገባዉ ነዳጅ ላይ የሚያደርጉትን ህገወጥነትን ለመከላከል ፖሊስ የሚያደርገዉን እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ እንዲደግፍ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዘግቧል፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *