የክልሉ መንግሥት ለኅብረተሰቡ የመንገድ የመሠረተ ልማት ጥያቄ የሰጠው ምላሽ እንዳስደሰታቸው ነዋሪዎች ተናገሩ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል “የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም” የበጀት ድጋፍ በኮንታ ዞን፣ ኮይሻ ወረዳ የተገነባው የደልባ-አልፋ ቶሊቃ የ12 ኪሎሜትር መንገድ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ተመርቀው አግልግሎት መብቃቱ ይታወሳል።

ከዚህ በፊት ወላድ እናቶችን ወደ ጤና ተቋም በቶሎ ለማድረስ አስቸጋሪ እንደነበረ የሚገልጹት የአከባቢው ነዋሪዎች አሁን ላይ የመንገዱ መገንባት ይህን ችግር መቀረፋን ተናግረዋል።

ያመረቱትን ምርት ወደ ገበያ እንዲያወጡ እንዳስቻላቸው የሚገልጹት የአከባቢው ነዋሪዎች በተላይ መንግሥት የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት ተንቀሳቅሶ እንዲያስከብር የመንገዱ መገንባት የጎላ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

የመንገዱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ መኾኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ አሁን ወላድ እናቶችን በአምቡላንስ ወደ ጤና ተቋም ከማድረስ ባለፈ በሞተር ሳይክል ከቦታ ወደ ቦታ በቀላሉ መንቀሳቀስ መቻሉን አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ በክልሉ ሁሉም ዞኖች በተለዩ ስድስት ወረዳዎች ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ወደ ተግባር መግባቱን ነው የክልሉ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የሁሉን አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ጌዲዮን እስጢፋኖስ የገለጹት።

መንገዱ ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት የገለጹት ሀላፊው ፥ ፕሮጀክቱ ከአለም ባንክ በተገኘ የበጀት ድጋፍ እንዲሁም 30 ከመቶ በክልሉ መንግሥት እና በየደረጃው ባለው መዋቅር የወጪ መጋራት ስርዓት መሸፈኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ቢሮ ስር በፕሮግራሙ ከ801 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ በጀት የአዳዲስ መንገድ ግንባታና የነባር መንገድ ጥገና ሥራ እየተከናወነ መኾኑን የገለጹት ኢንጅነር ጌዲዮን ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *