መሠረት ልማትን በሁሉም አከባቢዎች በማስፋፋት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው- ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ በኮንታ ዞን፣ ኮይሻ ወረዳ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀው ከፍተዋል።

በምረቃው መርሐግብር ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ዕሴት የኾነውን መሠረተ ልማት በሁሉም አከባቢዎች በማስፋፋት የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዞኑ ከዚህ በፊት በመንግስት እና በኅብረተሰብ ትብብር ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ አሁን ላይ የተገነቡ ፕሮጀክቶችም በአከባቢው ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ እንደኾነ ጠቁመዋል።

የኮንታ ኮይሻ ወረዳ ለሰፊ የእርሻ ምርት አመቺ አካባቢ እንደኾነ የገለጹት ዶ/ር ነጋሽ፥ የደልባ-ቶልካ መንግድ መገንባት ቀበሌን ከማዕከል ጋር ከማገናኘት ባለፈ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ እንደኾነ ተናግረዋል።

አከባቢው ከኮይሻ የሀይል ማመንጫ ተጠቃሚ ለማድረግ በፌዴራል መንግሥት የተሰጠው አውንታዊ ምላሽ ለአከባቢው ተጨማሪ ዕድል መኾኑንም ዶ/ር ነጋሽ ገልጸዋል።

በኮይሻ ከተማ አግልግሎት ይሰጥ የነበረውን የመስክ ሆስፒታል ደረጃ በማሻሻል የተሟላ የህክምና አግልግሎት ለመስጠት የጥናት ስራዎች እየተከናወነ እንደኾነም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመጨረሻም የለውጡ መንግሥት ለህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች እየሰጠ በጎ ምላሽ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው፥ ፕሮጀክቱ በከተማዋ ይስተዋል የነበረው የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር የሚቀርፍ መኾኑን ተናግረዋል።

የኮይሻ ንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት 11ሺህ 646 ነዋሪዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግም አስረድተዋል።

ፕሮጀክቱ 500 ሜትር ኩብ ውሃ መያዝ የሚችል ማጠራቀሚያ፣ 9.55 ኪ.ሜ የርዝመት የውሃ ማከፋፈያ መስመር እና 3.23 ኪ.ሜ የውሃ መሳቢያ መስመር ያካተተ ሲኾን ማህበረሰቡ በቀላሉ ውሃ የሚያገኝባቸው 10 የህዝብ የውሃ መጠጫ ቦኖችን ያካተተ ስለመመሆኑ ገልጸዋል።

በክልሉ ተጨማሪ የ27 አዳዲስ የውሃ ፕሮጀክቶች የጥናትና ዲዛይን ስራዎች መጠናቀቁን የገለጹት ሀላፊው ወደ ተግባር ስገባ የክልሉ የዋሃ ሽፋን የሚጨምር ነው ብለዋል ኢንጂነር በየነ።

በክልሉ ምሥረታ ወቅት ከነበረበት 32 ከመቶ አሁን ላይ ክልላዊ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሽፋን መድረሱን የገለፁት ኢንጅነር በየነ በዚህም ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቅ ኅብረተሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ከክልሉ ምሥረታ ወዲህ በዞኑ ያደሩ የህዝብ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ ስለመኾኑ የገለጹት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ናቸው።

በዞኑ በየደረጃ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በነቃ የኅብረተሰብ ተሳትፎ በልዩ ትኩረት እየተከናወነ የገለጹት አቶ ተስፉ በዚህም የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተግባር መፍታት መቻሉን አብራርተዋል።

የኮንታ ኮይሻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማርቆስ ወንድሙ በበኩላቸው የክልሉ መንግሥት ለወረዳው የህዝብ የልማት ጥያቄ ለሰጠው ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል።

በዕድገቱ በዛብሀ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *