የኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ዕቅድን ለማሳለጥ ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ግንዛቤ መፍጠር መቻሉ ተገለፀ።

Spread the love

የኢንተርፕሪነርሽፕ እና ኢኖቬሽን ሀሳብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለቦንጋ ዩንቨርስቲ መምህራን እና አካዳሚክ የስራ ሃላፊዎች እየተሰጠ ነው ፡፡

በኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ኘሮጄክቶች አስተባባሪ እና አሰልጣኝ አቶ ኢዮብ እምሩ እንደተናገሩት፣የኢንትርፕሪነርሽፕ እና ኢኖቬሽን ሃሳብ ይበልጥ እንዲሰርጸና ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጣ የግንዛቤ ስራ ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጐች በስራ ዕድል ፈጠራ፣በገበያ ትስስር እና ቢዚነስ ስራዎች ላይ ስልጠና መሰጠቱንም ተናግረዋል።

ስልጠና ከወሰዱት ውስጥ በቢዚነስ ውስጥ ከነበሩት 1ሺህ 4መቶ ዜጎችን ከባንክ ጋር በማስተሳሰር ከነዚህም ውስጥ ሰባት መቶ የሚሆኑ ዜጎች ከመቶ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ በማግኘት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።

የቦንጋ ዩንቨርስቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር አጥናፉ አስፋው በበኩላቸው፣ለተመራቂ ተማሪዎች በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ስልጠና መሰጠቱን ጠቅሰው አሁን ለዘርፉ አካላት እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በርካታ የሰው ሃይልን በማብቃት የተቋማትን አቅም ለመገባት የሚያስችል ነው ።

በኢንተርፕሪነርሽፕ እና በኢኖቬሽን ሀሳብ የሰለጠኑ የዘርፉ ሞያተኞች ተግባራዊ ልምምድ የሚያገኙበት እንደሆነም አስረድተዋል።

የኢንተርፕሪነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከቦንጋ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ባዘጋጅው በዚህ ስልጠና ላይ 60 የዩንቨርስቲ መምህራን እና የአካዳሚክ አመራሮች ናቸው እየተሳተፉ የሚገኙት፡፡

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *