ማዕከሉ በተመረቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ በክልሉ ለሚገኙ በርካታ ደንበኞች የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ

Spread the love

‎የደቡብ ምዕራብ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በተመረቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለ318 ደንበኞች የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠቱን የክልሉ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከል ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አህመድን አወል ገልጸዋል

‎በማዕከሉ በገቡ በ5 የክልልና በ4 የፌዴራል ተቋማት ስር የሚገኙ 28 አገልግሎቶችን በተቀላጠፈ መልኩ በአንድ ማዕከል ለዜጎች እየተሰጠ መሆኑም ተጠቁሟል።

‎ማዕከሉ በተመረቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ 318 አካላት የጤና ቢሮ፤ የንግድ ቢሮ፤ የኢትዮ ቴሌኮም፤ የፖስታ ቤት እና ገቢዎች ቢሮ አገልግሎት ያገኙ መሆናቸውንም አቶ አህመድን ገልጸዋል።

‎ማዕከሉ ከዚህ ቀደም ይስተዋሉ የነበሩ የዜጎች አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ከመቅረፍ ባሻገር በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣንና ዲጂታላይዝድ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ምክትል ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

‎ዜጎች ወደ ተቋሙ በመምጣት ጊዜ፣ ገንዘብና እንግልት የሚቀንሰውን የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን አለባቸው ሲሉም አቶ አህመድን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *