




በውይይት መድረኩ የቦንጋ ማዕከል የኢኮኖሚ ዘርፍ የብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ እና የክልሉ ቡና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የልማትና ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ኮጁአብ እንዳሉት ውይይቱ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ በአመራሩ እና በአባሉ ዘንድ የጋራ አረዳድና ተግባቦት ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል።
ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ ሀገር መንግስት ለመፍጠር ፓርቲያችን ያስቀመጠውን ግብ ተግባራዊ በማድረግ አመራሩና አባሉ ሚናውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
አመራሩና አባሉ የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት ከግብ እንዲደርስ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመተግበር የመሪነት ሚናቸው እንዲወጡ ጠይቀዋል።
ፓርቲው በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎችና ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በግብርና፣በኢንደስትሪ፣በቱሪዝም በማዕድን እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ የተጀመሩት የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ልማት ህዝቡንና ሀገርን የሚያሻግር በመሆ በጉባኤው ለተቀመጠው አቅጣጫ ተፈጻሚነት ከወትሮው በተለየ መልኩ መትጋት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት የተጀመሩት ኢኒሼቲቮች ከብልጽግና ህብረት ኢኮኖሚ ዘርፍ ጋር የሚሰናሰን በመሆኑ ሁሉም በየተግባር ዘርፉ በጊዜ የለንም መንፈስ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የበጎነት እሴት የሆነው የፓርቲው ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫዎች የተገኙትን ስኬት እንደ መስፈንጠሪያ አቅም በመጠቀም በቀጣይ ሰውኛ ተግባራትን በላቀ ተየሳሽነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የተጀመረው የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ ህዝቡ በምንሰጠው አገልግሎት እርካታ እንዲያገኝ እና የሚገባውን አገልግሎት ለማግኘት እንዲችል በየደረጃው ያለ አመራርና አባል በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገበል ሲሉ አስገንዝበዋል ።
ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትን/እኅትማማችነትንና ዐርበኝነትን እሴቶችን እንዲጎለብቱ ብርቱ ትግል ማድረግ ይጠበቃል ነው ያሉት።
ነጻ፣ ገለልተኛና ብቃት ያላቸውን ተቋማት በማባዛት የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሥራችንን በጠንካራ መሠረት ላይ ለማቆምና ጠንካራ የዴሞክራሲ ባህል ለመፍጠር በትኩረት መስራት አለብን ሲሉ አቶ በላይ ገልጸዋል።
የተጀመሩት የማህበራዊ ልማት ስራዎቻችን ግብን እንዲመታ በትብብር መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
