







የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ከክልሉ የምግብና ስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ሲያካሄድ የነበረው የሰቆጣ ቃል ክዳን ፕሮግራም የ2017 ዓ.ም የአፈፃፀም ግምገማና የ2018 የጀት ዓ.ም የዕቅድ ዝግጅት መድረክ ተጠናቋል፡፡
በመድረኩ በፕሮግራሙ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆኑ ከሪፓርቱ ለመመልከት የተቻለ ሲሆን በስርዓት-ምግብ ችግር የህፃናት መቀንጨርና የመቀጨጭ ለመቀነስ ፕሮግራሙ በታቀፉ ወረዳዎች ትኩረት ተሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተመልክቷል ።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ እንደተገለፁት፤ የሰቆጣ ቃልክዳን ፕሮግራም መንግሥት የምግብ ዋስትናን የሚያረጋገጥበት መንገድ በመሆኑን ተግባሩ እንደክልል ትኩረት ተሰጥቶ እየተመራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በፕሮግራሙ በታቀፉ ወረዳዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሥርዓተ ምግብ ሥርዓተ ምግብ ተኮር ዕቅድ በማቀድ በየሴክተሮቻቸው ሥራውን በባለቤትነት መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ በቂ እውቀትና ግንዛቤ በመያዝ ወደ ስራ በመግባት የተሻለ አፈፃፀም ለማምጣት ከወዲሁ መዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን አንስተው በተቋማት ድጋፍና ክትትል ሂደት ውስጥ የሰቆጣ ቃልክዳን ፕሮግራም የዕቅዱ አንዱ አካል ተደርጎ መተግበር እንደሚገባ ተናገረዋል፡፡
የክልሉ የምግብ ሥርዓት ማስተባባሪያ ዩኒት አስተባባሪ አቶ ማትዮስ ማልዳዬ፤ የሰቆጣ ቃልክዳን ፕሮግራም ለውጥ እየመጣ እና ትኩረት ማግኘቱን ገልጸው በክልሉ መቀንጨርንና መቀጨጭ በመቀነስ የተመጣጠነ ምግብ የሚመገቡ ህፃናት ቁጥር ከፍ ማለት አለበት ብለዋል፡፡
የሪፖርት አላለክና ከእቅድ ዝግጅት አኳያ የሚስተዋለውን መሠረታዊ ችግሮችን መስተካከል ለዘርፉ ተግባር ውጤታማነት ጥረት ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
የክልሉ እናቶችና ህፃናት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሠረት ወ/ማሪያም በበኩላቸው የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም በማጠናከር ከሥርዓተ ምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ የሚመጡ የመቀንጨርና የመቀጨጭ ችግሮችን ለመቅረፍ በሰቆጣ ቃል ክዳን ማስፋፊያ ፕሮግራም የታቀፉ ወረዳዎች እና ሴክተር መ/ቤቶች በቅንጅት መሥራት አስፈላጊ ነው ብለዋል ።
አቶ መሠረት አክለውም የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራሙ ዕቅድ ሲታቀድ ግልጽና ሊያሰራ የሚያስችል፣ ችግር ፈቺ እንዲሁም ታችኛውን ማህበረሰብ መለወጥ የሚያስችል መሆን እንዳለበት ተናግረዋል ፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የፕሮግራሙ በጀት በወቅቱ ያለማውረድ፣ ቅንጅታዊ አሰራር ችግር መኖሩንና በአተገባበር ወቅት የሚታዩ ውስንነቶች በተገቢው ተለይቶ ከተሰራ ከዚህ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል አንስተዋል፡፡
የዘርፉ ተግባር የብዝሃ ተቋማት የጋራ ስራን የሚጠይቅ በመሆኑ የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ፕሮግራሞችን ውጤታማነት በየጊዜው ክትትልና ግምገማ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
