በክልሉ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁ ተገለጸ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበጎ ፈቃድ ስታንዳርድ እና ትመና ላይ ለዞን አመራሮች እና ባለሙያዎች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

በዘንድሮው የክረምት ወጣቶች በጎ ፍቃድ አግልግሎት ከ2.4 ሚሊዮን በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጎ ፍቃድ አግልግሎት ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ሥራ መጠናቀቁን ነው የክልሉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ሌዊ የገለጹት።

በበጎ-ፍቃድ አግልግሎቱ ከተለያዩ ማህበራዊ መሠረት ከ1 ሚሊዮን በላይ በጎ ፍቃደኞች በቀጥታ እንደሚሳተፉ የገለጹት ኃላፊዎ፥ ከዚህም አሀዝ ውስጥ ከ6መቶ ስልሳ ሺህ በላይ የሚኾኑት ወጣቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።

የክረምት በጎ ፍቃድ አግልግሎት ወጣቶች በክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አውንታዊ ለውጥ ሂደት ውስጥ ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡ በማድረግ የማኅበረሰቡን በጎ ዕሴት እንዲያጎለብቱ ዕድል የሚፈጠር እንደኾነም ነው ወ/ሮ ራሄል የጠቆሙት።

በዘንድሮው የበጎ ፍቃድ አግልግሎት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በየደረጃው ባለው መዋቅር በቂ ዝግጅት መደረጉን ያብራሩት ኃላፊዎ ቅንጅታዊ አሰራርን በመዘርጋት ለውጤታማነቱ በትብብር መሠራት ይገባል ብለዋል።

ወጣቶች ጊዜያቸውን፣ ጉልበትና እውቀታቸውን ለማኅበረሰብ ሁለንተናዊ ለውጥ መስዕዋት ለማድረግ በተለመደው መልኩ ራሳቸውን ከወዲሁ ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው የገለጹት ወ/ሮ ራሄል ባለፋት ዓመታት በዘርፉ የተመዘገበው ውጤት አመርቂ መኾኑን ተናግረዋል።

በ2017 የክረምት በጎ ፍቃድ አግልግሎት በ14 ዘርፎች በክልሉ በወጣቶች የላቀ ተሳትፎ ከ9መቶ 80 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የበጎ ፍቃድ አግልግሎት እንደሚከናወንም ነው በመድረኩ የተገለጸው።

ባለፉት ዓመታት በቢሮው አስተባባሪነት በየደረጃው በተከናወኑ የበጎ ፍቃድ አግልግሎት ከመንግሥትና ከህዝብ ለውጣ የሚችል በርካታ ሀብት ማዳን መቻሉም ተገልጿል።

በቢሮው የወጣቶች ማካተት ዳይሬክተር አቶ በላይ በቀለ ዝርዝር የበጎ ፍቃድ አግልግሎት ስታንዳርድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *