በጤናው ዘርፍ ሀሩራማ አካባቢዎች የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል ትኩረት በመስጠት ሊሰራ ይገባል ተባለ

Spread the love

የተቀናጀ እና የተሻሻለ የኦንኮ ሰርኪያሲስ በሽታን ማስወገጃ እና ብሔራዊ የጊኒ ዎርም ማጥፋት ፕሮጀክት የማስተዋወቅ መድረክ በሚዛን አማን ተካሂዷል።

በፕርግራሙ ማስተዋወቅ መድረክ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ በክልሉ በ5 የተለያዩ በሽታዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱን ተናግረዋል ።

የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት በሰሯቸው ስራዎች ውጤታማ ተግባራትን አከናውነዋል ብለዋል አቶ ሀይሌ።

በክልሉ የኦንኮ ሰርኪያሲስ በሽታን ለማጥፋት በተሰራው ስራም ከፍተኛ ውጤት መገኘቱንም አብራርተዋል ።

የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ በክልሉ በኦንኮ ሰርኪያሲስ፣በጊኒ ዎርምና በዝሆኔ በሽታዎች ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራም እንደሚገኝ አቶ ሀይሌ ገልጸዋል።

በዚም በክልሉ በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳና ማጂ ወረዳ የጊኒ ዎርም በሽታን ለመቆጣጠርና ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

የካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ በክልሉ ባለፉት 5 ዓመታት በሰራው ውጤታማ ተግባር በክልሉ መንግስት ስም አቶ ሀይሌ ምስጋናቸውን አቀርበዋል ።

ባለፉት 5 ዓመታት በክልሉ በኦንኮ ሰርኪያሲስ፣ በጊኒ ዎርምና ዝሆኔ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተሰሩ ስራዎች ቀርበዋል።

በክልሉ በቀጣይ 5 ዓመታት ለሚከናወኑ የተቀናጀ እና የተሻሻለ የኦንኮ ሰርኪያሲስ በሽታን ማስወገጃ እና ብሔራዊ የጊኒ ዎርም ማጥፋት ፕሮጀክት የማስተዋወቅ ፕሮግራም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

በዚሁ የትውውቅ መድረክ የክልሉ ጤና ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ የካርተር ሴንተር አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ የዞንና የወረዳ የጤና ባለሙያዎች እና ብሔራዊ የጊኒ ዎርም ማጥፋት ፕሮጀክት አስተባባሪ ተገኝተዋል።

በፕሮግራሙ የካርተር ሴንተር መስራች ለሆኑት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ተደርጎላቸዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *