የትምህርት ሚኒስቴር
በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ በድረ-ገፅ ወይም በአጭር የፅሁፍ መልእክት አማካኝነት መመልከት እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ገልጸዋል፡፡
የ2015 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ሚኒስትሩ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፤ የ2015 የትምህርት ዘመን የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ 848 ሺህ 99 ተማሪዎች ውስጥ 27 ሺህ ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልፀዋል።
ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 3.2 ከመቶ ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸውን የገለፁት ሚኒሰትሩ፤ ያለፉት ተማሪዎች ቁጥር ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ0.01 መቀነሱን ተናግረዋል።
ዘንድሮ 3 ሺህ 106 ትምህርት ቤቶች ፈተና ያስፈተኑ ሲሆን፣ ከነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 328 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በዚህም 42.8 ከመቶ ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸው ነው የተገለፀው።
የዘንድሮው ፈተና ከተፈጥሮ 649 ከ700 ሆኖ ተመዝግቧል። ውጤቱን ያስመዘገበችው ተማሪ ሴት መሆኗም ተነስቷል።
በማህበራዊ ሳይንስ 533 ከ600 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡም ተገልጿል።
ፈተናውን የተፈተኑ ተማሪዎች ከነገ ጠዋት 12 ሰአት ጀምሮ ውጤት ማየት እንደሚችሉም ተገልጿል።
Ebc
