የብልፅግና ፓርቲ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

Spread the love

በአጠቃላይ ሀገራዊ ፓለቲካ ሁኔታ፣ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ለማሳካትና በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ የንቅናቄ አጀንዳዎችን የሚገመግመው መድረክ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ተጀምሯል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የዘርፍ አመራሮች የክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል የአደረጃጀት እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ለ3 ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ መርሀ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንትና የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ እንደገለፁት በመድረኩ የፓርቲ መደበኛ ስራዎች፣ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ግብረ መልስ እና በየክልሉ ያሉ የፓለቲካ አዝማሚያ ግምገማ እንደሚደረግ አንስተዋለደ።

በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ በየደረጃው የተደረጉ ውይይቶች አፈጻጸም በተመለከተ ውይይት ይደረጋልም ብለዋል።

በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ የሚደረግ ሲሆን በስራ እድል ፈጠራ፣ ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የሚከናወኑ ስራዎች እና ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ያሉበት ደረጃ በስፋት የሚገመገም መሆኑን ክቡር አቶ አደም ፋራህ ገልፀዋል።

#prosperity

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *