




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የወሳኝ ኩነቶች ዘርፍ ከክልል ቢሮ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት የጋራ ምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት፤የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እንደተናገሩት፤ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ እና አስተዳደራዊ ዘርፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና አለዉ ብለዋል፡፡
ለሀገራችን ልማት እድገትና ብልጽግና መረጋገጥ ታዓማኒነት ያለዉ መረጃ ለማደረጀት የሚረዳ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ እንዳሉት፤መንግስት ከለዉጡ ወዲህ ሰዉ ተኮር ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ አሰራር ተላቆ በዘመናዊ መልክ እየተደራጀ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
ለሀገራችን ልማትና ዕድገት ተዓማኒነት ያለዉ መረጃ ለማደራጀት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት አቶ በላይ በተለይ ከፍቺ፣ ከጋብቻ፣ ከልደት እንዲሁም ከማህበራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ኩነቶች እንዲመዘገቡ እና የጠራ መረጃ እንዲኖር የወሳኝ ኩነት ዘርፍ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለዉጤታማነቱም ተቋማት የጋራ ተሳትፏቸዉን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት በክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የጸጥታ ዘርፍ ምክትልና የወሳኝ ኩነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደነቀ እየቀረበ ይገኛል፡፡
በካሳሁን አሰፋ
