




በምዕራብ ኦሞ ዞን የለዉጡን መንግስት 8ተኛ አመት አስመልክቶ የሚደግፍ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በጀሙ ከተማ ተደርጓል።
በመድረኩ የክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንደተናገሩት እሩቅ አልሞና አሻግሮ የማየት የንስር ዐይን ዕይታ ያለው የለወጥ መንግስት በኢኮኖሚ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ዘርፎች ለማሳካት ያሰበውን ህልሞች ለማሳካት ህዝቡ መደገፍ አለባቸው ብልዋል።
የለዉጥ መንግስት የተናገረው የሚፈጽም የጀመረውን በተግባርና በዉጤት የሚያሳይ ለትዉልድ የሚሰራ መንግስት መሆኑ አቶ ፋጂዮ ተናግሯል።
ወቅቱ 7ተኛ ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ የሚካሄድበት በመሆኑ ህዝቡ የመራጭነት ካርዲ በመዉሰዲ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተጠቅሞ የዜግነት ግዴታ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ በበኩላቸው የለዉጥ መንግስት ትሩፋቶች ከእጅግ ብዙ በጥቂቱ ለአብነት የክልላችን የመዋቅር ጥያቄ፤የዞናች የመዋቅር ጥያቄ የጀሙ ከተማ የባቹማ ፤የማጂ ቱም ከተሞች እና የጎሪ ጌሻ፤ የጋቺት ወረዳ የመዋቅር ጥያቄ ምላሾች ያገኙት በለዉጡ መንግስት መሆኑ ገልጸዋል።
የመደመር መንግስት የበለጸገች ኢትዮጵያ የመገንባት ራዕይ መሰረተ የሆነው የግብርና ገጠር ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ሥር ነቀል ለዉጥ ምሶሶ ብሎ ያምናል ነዉ ያሉት።
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር ለማሸጋገር የተደረገ ርብርብ ከፍተኛ ዉጤት መመዝገቡ ተናግሯል።
የጀሙ ከተማ ከንቲባ አቶ ሺፈራው ማናባ አክለው የለዉጥ መንግስት አካታችኋል የፖለቲካ እውን ያደረገበት ሀገር በታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች እንዲትሸበርቅ ያደረገ መሆኑ ገልጸዋል።
በዚሁ በለዉጥ የከተማዉ አስተዳደር በመዋቅር የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት መሆኑ አስገንዝበዋል።
በድጋፍ ሰልፍ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ እና የተለያዩ መፈክሮች በማሳየት ከመንግሥት ጎን የሚቆሙበት እና የለዉጡ መንግስት አድንቋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
