በዘንድሮ የመኸር ምርት ዘመን በክልሉ ከ391 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 17 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ይሰራል፡- አቶ ማስረሻ በላቸው

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የ2015/16 ዓ.ም የመኸር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2016/17 ዓ.ም የመኸር ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በንቅናቄው መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የልማት በክልላችን ግብርና ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ ተግባራት መከናወን በመቻላቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ እየመጣ ያለ መሆኑን መገንዘብ ችለናል ብለዋል።

አቶ ማስረሻ አክለው ክልሉ በዘንድሮ የመኸር ምርት ዘመን በክልሉ ከ391 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 17 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ግብ መጣሉን ተናግረዋል።

በክልሉ በሰብልና በሆርቲ ከልቸር ምርት ከ880 ሺህ ሄክታር በላይ ማሣ በሰብል በመሸፈን 55 ሚሊዮን ኩንታል ገደማ ምርት ለመሰብሰብ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ እንደለም ተናግረዋል፡፡

እስከአሁን ከ25 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የገለጹት አቶ ማስረሻ ቀሪው በአጭር ጊዜ ለመሰብሰብ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በክልሉ የምርት እድገት ለማምጣት በአከባቢው ያሉ ያልተናኩ መሬቶችን ወደ ምርት ስርዓት ውስጥ ማስገባት እና ባለን ምርት ላይ ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የምርትና ምርታማነት ማነስ ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ በትኩረት እንደሚሰራ ተነግሯል።

ባለን ምርት ላይ ምርታማነትን ለማረጋገጥ እስከ አሁን 168 ሺህ ኩንታል ወይም ከአጠቃላይ 68% የሚሆን አፈር ማዳበሪያ መጠቀም የተቻለ መሆኑን አቶ ማስረሻ ገልጸዋል።

በአሁኑ ሰዓት የክልሉ የ2015/16 ዓ.ም የመኸር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና እርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፌ እየቀረበ ይገኛል፡፡

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ የዞንና የወረዳ የመንግሥት ተጠሪዎች እንዲሁም የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *