




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ደን ፣አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ በደን መመናመንና መጨፍጨፍ የሚከሰቱ አማቂ ጋዞች ቅነሳ ፕሮግራም ( REED+) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በደን ተኮር ኑሮ ማሻሻያ አማራጮችና ንብ ማነብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫና የልምድ ልውውጥ በቦንጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታመነ በቀለ ክልሉ ባለው የተፈጥሮና ሰውን ሰራሽ ደን ሃብት የማር ምርትን በጥራትና በብዛት ለማምረት የሚያስችል አቅም አለው ብለዋል።
በክልሉ በ330 ቀበሊያት 970 የንብ መንደር የሚገኝ ሲሆን አንድ አርሶ አደር አምስት ዘመናዊና አምስት ባህላዊ የንብ ቀፎዎች እንዳኖሩት በተሰራው ስራ ከዛሬ ሁለት አመት በፊት ይገኝ ከነበረው 56ሺህ ቶን ወደ 69 ሺህ ቶን የማር ምርት ማግኘት መቻሉን ጠቅስዋል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ክልሉ በዓመት አራት ጊዜው የማር ምርት ሊያስገኝ የሚያስችል አቅም አለው በመሆኑ ዘርፉ አሁንም ተከታታይ ስራ ይፈልጋል ብልዋል ።
በደን ተኮር የህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራሞች በመታገዝ በማር ምርት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ያለውን ስራ ለማሳለጥ
የዘርፉ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ለቀጣይ ተግባራት በእውቀት እንዲያከናውኑ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ተረድተው በብቃት መከታተልና መሳትፍ እንደሚገባቸው አሳስበዋል ፡፡
REED+) ኢትዮጵያ በዋናነት አትኩሮ የሚሰራው በደን አጠባበቅና ልማት እንድሁም የህብረተሰቡን ኑሮ ማሻሻል ላይ መሆኑን የገለጹት የክልሉ ሬድ ፕላስ ኢንቨስትመንት ፕሮግራም አስተባባሪ ዶ/ር የርቾ ብርሃኑ የመድረኩ ዓላማ ግንዛቤ በመፍጠርና ልምድ በመለዋወጥ የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ከፍ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
የ29 ወረዳዎችና የአምስት ክላስተር ፕሮግራም አስተባባሪዎችና ከስድስት ዞኖች ለመጡ የንብ እርባታ ባለሙያዎች በደን ተኮር ኑሮ ማሻሻያ አማራጮች፣በንብ ማነብ አተገባበር ክፍተትና በውጤታማ የዕቅድ አስተቃቀድ ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በውቢት ደበበ
