
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢን እና የሥራ አመራር አባላትን ሹመት አፅድቋል።
6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4 አመት የስራ ዘመን 36ኛው መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ አቶ ተስፋዬ ንዋይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል፡፡
እንዲሁም አቶ ተክሊት ይመስል እና ወ/ሮ ነሲም አሊ የምርጫ ቦርድ የሥራ አመራር አባል ሆነው ተሹመዋል።
ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ጉዳይ ጋር ተያይዞ የቀረበን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሰው ሀብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።
የዕፅዋት ጥበቃና ኳራንታይን የተዘጋጀን ረቂቅ አዋጅ እንዲታይ ለግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመሉ ድምጽ ተመርቷል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
