በሚዛን አማን ከተማ የወጣቶች ክንፍ የውይይት መድረክ ይካሄዳል

Spread the love

በሁለተኛ የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ላይ የክንፉ አመራር፣ አባላትና ደጋፊዎች የሚሳተፉበት የውይይት መድረክ ከመጋቢት 15/2017 ዓም ጀምሮ በሚዛን አማን ከተማ ይካሄዳል።

የውይይት መድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ገለጻ የሰጡት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ወጣት ወንዱ መንገሻ አስታውቀዋል።

ጉባኤው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎችና ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ላይ ግልጸኝነት፣ የጋራ አረዳድና መግባባት ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ውይይት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ወጣቶች የሀገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት የጀርባ አጥንት መሆናቸውን ፓርቲያችን ያምናል ያሉት ም/ኃላፊው የወጣቱን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ሊያጠያክር የሚችሉ በሁለተኛ የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች መቀመጡን ገልጸዋል።

በዚህም በየደረጃው የሚገኙ የብልፅግና ወጣቶች ክንፍ አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊ ወጣቶች የጉባኤው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በሚገባ ተግባራዊ በማድረግ ፓርቲያችን የሀገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጉዞ ከምንጊዜውም በላይ ርብርብ በማድረግ የፓርቲያችን ገዥ ትርክት የሆነው ብሔራዊነት አስተሳሰብ ለመገንባት በተደራጀ መንገድ መረባረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የወጣቶች ክንፍ መዋቅር ጠንካራና ተልዕኮውን በውጤታማነት መወጣት እንዲችል አብሮነትንና አንድነትን በማጠናከር ለላቀ ስኬት መትጋት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በተዋረድ ግለቱን የጠበቀ ውይይት እንደሚደረግ የገለጹት ኃላፊው በአጠቃላይ ከ230 ሺህ በላይ የክንፉ አመራር፣ አባላትና ደጋፊዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *