



ድጋፉን ያስረከቡት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንዳሉት አምቡላሶቹ የእናቶችና ህጻናት ጤናን ለማጎልበት እንዲሁም ለድንገተኛ ህክምና አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸውን ገልፀዋል ።
በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት ለማህበረሰቡ ጥራት ያለውን አገለግሎት እንዲሰጡ ለማገዝ ቢሮው አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በክልሉ የጤና አገለግሎቶችን ይበልጥ ለማጎልበትና ተደራሽነትን ለማስፋት ሁሉም የባለድርሻ አካላት ሊተጉ እንደሚገባ ኃላፊው አስገንዝበዋል።
ተሽከርካሪዎቹ የእናቶችንና ህጻናት ጤናን ለማስጠበቅ እየተካሄደ የሚገኘውን ተግባር በእጅጉ እንደሚያግዙ እና
አገልግሎቶቾንም ለማቀላጠፍ ሚናቸው የላቀ እንደሚሆን ያነጋገርናቸው የዞን ጤና መምሪያ ኃላፊዎች ገልፀዋል።
አምቡላሶቹ በወጣላቸው የአጠቃቀም ደንብ መሠረት ለተፈቀደላቸው አገልግሎቶች ብቻ መዋል እንዳለባቸውና ለዘላቂ ተጠቃሚነትም ተገቢ የሆነ ክትትል ሊደረግ ይገባል ተብሏል።
