


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የትራንስፎርሜሽን ሪፎርም እና የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ በመድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የፍትህ ሪፎርም ስራ ሀገራዊ የለውጥ ሂደትን ተከትሎ የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጀመረ እና ውጤት እየተመዘገበበት ያለ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
የፍትህ ዘርፋን የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የህብረተሰቡን ፍትህ የማግኘት መብት በማስከበር የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መንቀሳቀስ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ እሸቱ ጎደቶ እንደተናገሩት ፣ቢሮው በህግ የተሰጠውን ተልዕኮ እና ሀላፊነት ተግባራዊ በማድረግ ህዝብና መንግስት የሚጠብቁትን ውጤት ለማሳካት የሚያስችል ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል ።
የፍትህ ዘርፋን አገልግሎት የበለጠ በማሻሻል በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እና ተዓማኒነት ያለው ተቋም በመፍጠር የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ የሪፎርም ስራዎች ላይ ርብርብ እየተደረገ እንዳለም አቶ እሸቱ ገልጸዋል።
በዚህም፣የክልሉ ፍትህ ዘርፍ ተቋማትም በክልሉ ውስጥ ፈጣን ፣ቀልጣፋ፣ውጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ የፍትህ አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን እርካታ የሚያሳድግ የፍትህ ስርዓት ለመፍጠር የሚያስችል የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ መነሻ ያደረገ የ3 ዓመት ክልላዊ የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱንም ተናግረዋል።
በመድረኩ የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተግባር አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል ።
በካሳሁን አሰፋ
