



በነዳጅ መስፈሪያ መሳሪያዎች ምርመራ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ ለባለድርሻ አካላት እየተሰጠ ነው።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ በነዳጅ መስፈሪያ መሳሪያዎች ምርመራ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት እየሰጠ ነው።
በዚሁ ስልጠና ላይ የተገኙት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ህገ_ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ድጂታል የስነ _ልኬት ስራዎችን እውን ማድረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።
የስነ _ልኬት ስራዎችን በክልሉ እውን ማድረግ ሸማቾች ትክክለኛና ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲሸምቱ ያስችላቸዋል ሲሉም ተናግረዋል።
ነዳጅ ከውጭ ሀገር የሚገባ ምርት ሲሆን ኢትዮጵያ ለዚሁ ምርት በ2016 ዓ/ም 4.2 ቢሊዮን ዶላር መክፈሏን አስታውሰዋል።
እየተስተዋለ ያለውን የነዳጅ ብክነት እና የኮንትሮባንድ ንግድ ወደ ዲጂታል ክፍያ ስርዓት በማሸጋገር የቁጥጥር ስራን በማጠናከር ህገ_ወጥነትን ለመከላከል ስልጠናው ትልቅ አቅም መሆኑንም አቶ ተመስገን ገልጸዋል።
በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ባለድርሻ አካላት እየተሰጠ ያለውን የክብደትና የነዳጅ ልኬት ስራዎች በክልሉ እውን ለማድረግ ስልጠናውን በአንክሮ ሊከታተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በዓለም አቀፍ ለ42ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ12ኛ ጊዜ
“ጥራቱን የጠበቀ ምርትና አገልግሎት ለሸማቾች” በሚል መሪ ቃል በዕለቱም ተከብሯል።
የቢሮ ኃላፊው አቶ ተመስገን ከበደ ለበዓሉም እንኳን አደረሳችሁ በማለት ሸማቹ ጥራቱን የጠበቀ ምርት የመግዛት እና ለገዛበትም ደረሰኝ የመቀበል ልምዱን በማዳበር ህገ_ወጥነትን ከመከላከል አንጻር የበኩሉን እንዲወጣም ጠይቀዋል።
እየተሰጠ ባለው ስልጠና ላይ የቢሮው አመራሮች ፣ባለሙያዎች እና ከሁሉም ዞኖች የተጠሩ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በታጠቅ አበበ
