Spread the love

በመኸር ከለማው የማሽላና በቆሎ ሰብሎች የተሻለ ምርት ይጠበቃል፦ የጨና ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በኩታ ገጠም በመኸር ከለማው የማሽላና በቆሎ አዝመራ የተሻለ ምርት ለማግኘት ማታቀዱን ወረዳው ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ጽ/ቤት አስታውቋል።

በካፋ ዞን ጨና ወረዳ በኩታ ገጠም በመኸር ከለማው የማሽላና በቆሎ አዝመራ የተሻለ ምርት ለማግኘት ማታቀዱን ወረዳው ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ጽ/ቤት አስታውቋል።

በወረዳው በ2017/18 የምርት ዘመን 8ሺህ 5 መቶ ሄክታር መሬት በላይ በተለያዩ የመኸር ሰብሎች መሸፈኑ ተገልጿል፡፡

በጨና ወረዳ በተለይም የዶሻ ጡጋ እና በጎታ ክላስተር ያሉ አርሶ አደሮች ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ሲያከናውን ቆይተዋል።

የአካባቢው አርሶ አደሮች ማሽላና በቆሎ ከመሳሰሉ ሰብሎች በተጨማሪ አትክልትና ፍራፍሬ አልምተው ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙም እየተደረገ ነው።

በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶ አደር አየለ አለሙና ገረመው ኃይሌ የተሟላ የግብርና ፓኬጅ በመጠቀም በኩታ ገጠም ያለሙት የማሽላና በቆሎ ሰብሎች የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አርሶአደሮቹ እንዳሉት፤ በኩታ ገጠም በመኸር ከለማው የማሽላና በቆሎ ሰብሎች የተሻለ ምርት ለማግኘት በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ።

ለዚህም ከወረደ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ከ3 እስከ 4 ወራት ውስጥ የሚደርስ 4 ዓይነት የማሽላ ዝሪያዎች ማግኘታቸውን ገልጸው አሁን ላይ ማሽላው በጥሩ ቁመና ላይ መገኘቱ ጥሩ ምርት እንደሚያገኙ ጠቁመዋል።

የጨና ወረዳ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዘኸኝ ጋኖ በወረዳው ካሉ 24 ቀበሌዎች በ13 ቀበሌያት የማሽላ ምርት በሰፊው የሚመሩት መሆኑንና በ2017/18 በመኸር እርሻ 2840 ሄክታር መሬት ማሽላ መሸፈኑን ገልጸዋል።

በወረዳው ጦሻ ጡጋ፣ አሉዋ፣ ዋንጃል እና በቦባ በላ ክላስተሮች ማሽላ እና በቆሎ ሰብሎችን በኩታ ገጠም በሰፊው በማምረት የሚታወቁ ቀበሌዎች መሆናቸውና የማሽላ ምርታማነቱ በሄክታር ከ50 እስከ 60 ኩንታል ምርት እንደሚሰበሰብ አንስተዋል።

አርሶአደሮች የምርት መጠኑን ለማሳደግ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀማቸው በመሆኑ ይህንንም እንደወረደ የማስፋት ስራ እየተሰራ መሆን ተናግረዋል።

ከ3 እስከ 4 ወራት ውስጥ የሚደርሱ 4 ዓይነት የማሽላ ዝሪያዎች መኖሩን ጠቁመው ቀጣይ ላይ በፕሮጀክቶች በማስደገፍ ምርታማነቱ በምርምር የተሻለ የማሽላ ዝሪያ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ የማድረግና የማስፋት ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት ዎንጃል በሚባል አካባቢ የማሽላ ምርት ወደ ገበያ እየወጣ እና በቀን ከ10 እስከ 15 መኪና የማሽላ ምርት ተጭኖ ለማዕከላዊ ገበያ እየተላከ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በወረዳው በ8 ቀበሌዎች በቆሎ በስፋት እንደሚመረት እና ጎታ እና ዶሻ ጡጋ ክላስተር በቆሎ በበልግ በሰፊው የሚመረትበት ነው ብለዋል።

በዶሻ ጡጋ ክላስተር 289 ሄክተር በቆሎ በኩታ ገጠም በሙሉ ፓኬጅ የሚመረትበት በኤቲአይ የተደራጀ 61 አባላት የያዘ ማህበር እንዳለም ጠቁመዋል፡፡

የገጠሩ አርሶ አደር ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የሚያግዙ ምርጥ ዘርና የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ በማድረግ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ መሰራቱን ገልጸዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን ምርጥ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱንም ጨምረው አስታውቀዋል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *