




የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ታደሰ ከክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ የህዝብ የልማት ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ በርካታ ተግባራት በወረዳው እየተከናወነ መኾኑን ተናግረዋል።
ወረዳው፣ በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ሰፊ የልማት አቅም ያለው ወረዳ መኾኑን የጠቆሙት አቶ ታረቀኝ ለግብርናና ለቅመማ ቅመም ልማት ሰፊ አቅም ያለው እንደኾነ አስረድተዋል።
ወረዳው በተለይም ለቡና ምርት ተስማሚ የአየር ፀባይና ስነምህዳር ያለው አከባቢ መኾኑን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው በዚህም በርካታ አርሶአደሮች ቡናን በጥራትና በብዛት በማምራት ተጠቃሚ መኾን መጀመራቸውን ተናግረዋል።
የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ የቡና ችግኞችን በማቅረብ ጭምር መንግሥት በትኩረት እየሰራ እንደኾነ የገለጹት አቶ ታረቀኝ በዚህም አመርቂ ውጤት እየተመዘገ ነው ብለዋል።
በወረዳው በአርብቶ አደር ቀጠና አልፎ አልፎ የሚስተዋለው የፀጥታ ስጋቶችን በመቅረፍ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ታረቀኝ የተጀመሩ ተግባራት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላል ብለዋል።
በቡና ምርት ከተሰማሩ አርሶአደሮች አንዱ የኾኑት አቶ ተካ ታመነ፥ የወረዳው መንግሥት በመሬት ምርጥ ዘር አቅርቦት እንዲሁም በባለሙያ ድጋፍ እየደገፈ እንደሆነ አስረድተዋል።
ምርቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የገለጹት አቶ ተካ የተገኘው ውጤት የወረዳው መንግሥት እያቀረበ ባለው ድጋፍ ታግዞ መኾኑን ገልጸዋል።
የወረዳው መንግሥት በገጠር የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ላይም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መኾኑን የገለጹት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በዚህም ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል።
በወረዳው የህዝብ የልማት አቅሞችን በማቀናጀት በመሠረተ ልማት ግንባታ መከናወኑንም አቶ ታረቀኝ ጨምሮ ገልጸዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
