




በቤንች ሸኮ ዞን “በመደመር መንግስት እይታ ለዘርፎች እምርታ” የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ይገኛል።
ከህዳር 22 እስከ 30/2018 በዞን ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘው የ3ኛ ዙር የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ማጠቃለያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን የስልጠና መድረኩን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት በሀሉም ዘርፎች እየተመዘገቡ የሚገኙ ውጤቶችን ከፓርቲው እሳቤ መነሻ በማድረግ የተከናወኑ ናቸው ብለዋል።
ስልጠናው በአመራሩ መካከል ያለውን የአመለካከት አንድነት ወደ ተግባር አንድነት ለመለወጥና ከፍ በማድረግ በገጠርና በከተማ ብልጽግናን እውን ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በገጠርና በግብርናው ዘርፍ ተግባራትን ትራንስፎርም የማድረግ እና በከተማ ከማኑፋክቸሪንግና ኢንዱስትሪው ጋር ማመጋገብ ያስፈልጋል ብለዋል።
ትስስሩን ለማጠናከር የአርሶ አደሩን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ማሳደግ ፣ ዘርፉን ከዝናብ ጥገኝነት ማላቀቅና በአመት ሁለቴና ከዚያ በላይ በማምረት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
እንደ ሀገር ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ በሚደረገው ሽግግር ውስጥ በየደረጃው የአመራሩ ሚና የጎላ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል። ከተሞችን ለኢንዱስትሪያሊስቶች ምቹ ማድረግ ፣ ዘርፉን በውጤት ማጀብ ይገባል ብለዋል።
ከተሞችን ለነዋሪዎቹ ምቹ ማድረግ ፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ በፕላን እንዲመሩ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። ከተሞች የአመራር ፕሮጀክቶች ናቸው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ዘርፉን በልዩ ትኩረት መምራት ይገባል ብለዋል።
ከተማና ገጠርን የቱሪዝምና የኮንፍረንስ ቱሪዝም በማድረግ ተጨማሪ የሀብት መፍጠሪ ማዕከላት እንዲሆኑ ማድረግ ድገባል ብለዋል። ያሉንን የባህል እሴቶች ፣ ቅርሶች ፣ ትውፊቶችና የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን በማልማት ወደ ሀብት መቀየር ይገባል ብለዋል። ቱሪዝም ያለፈውን ከአዲሱ ትውልድ ጋር ለማስተሳሰር ያለው አቅም ከፍተኛ በመሆኑ እንጠቀምበት ብለዋል ሲል የቤንች ሸኮ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
