




በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ ”የዘርፎች እምርታ” በሚል ሃሳብ ለመካከለኛው አመራር በየማዕከሉ ላለፉት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ3ተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራር የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰልጣኞች በየዞኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጉብኝ አደርገዋል።
የጉብኝቱ ዓላማ ሰልጣኝ አመራሮች ከስልጠናዉ በተጓዳኝ በክልሉ ውስጥ በተለያዩ አካባቢ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በመጎበኘት ልምድ ልውውጥና ተሞክሮ በመቀመር በየአካባቢው ወደ ተግባር ለመቀየር ታሳቢ ያደረገ ነው።
የካፋ ዞን መካከለኛ አመራሮች በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ አስተዳደር የተሰራ የኮሪደር ልማት ስራን፣ በጠሎ ወረዳ የበጋ ቀበሌ የአቶ አየለ ወ/ጊዮግስ ቡና ልማትና ግሮን አልቦነ የወጣቶች የዶሮ እርባታ ጉብኝት አደርገዋል።
የሸካ ዞን ሰልጣኞች በየኪ ወረዳ ምርቱን ወደ ወጪ ገበያ ለማቅረብ በአንድ ወጣት እየለማ የሚገኝ 9ሺ ሄክታር ቁንዶ በርበሬና የቫኔላ ምርት፣የቡና ጥራትን ለማስጠበቅ በወረዳው በህብረት ቀበሌ በአቶ አሸናፊ በላይ እየተተገበረ ያለውን የኳሊቲ ኮፊ ዝግጅት በሰልጣኞቹ ጉብኝት ተደርገዋል።
በቤንች ሸኮ ዞን የኮሊደር ልማት፣ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደሩ የማህበረሰብ መድሐኒት ቤት፣ ልማት ለሰላም የዶሮ እርባታ መንደር፣ የምክር ቤት ህንጻ ፣የአማን የኮሊደር ልማት፣ አማን 1ኛ ደረጃ ሞዴል ቅድመ መደበኛ ት/ቤት ስራዎችንም ምልከታ አድርገዋል።
በምዕራብ ኦሞ ዞን ሰልጣኞች በጀሙ ከተማ የሚገኘውን የጥላሁን ተሰማ የቡና መፈልፈያ ኢንዲስትሪ እና የጀሙ ሞዴል ቅድመ 1ኛ ትምህርት ቤት ጉብኝት አድርጓል።
የዳውሮ ዞን መካከለኛ አመራሮችም በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር እየተሠራ ያለውን የዳውሮ ባህል ማዕከል ግንባታ፣ የዳውሮ ብሔረሰብ ኢትኖግራፊክ ሙዚዬም፣ የዶሮ ክላስተር፣ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዟዙረው በመጎብኘት ላይ ናቸው።
በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በንድፌ ሀሳብ ሲሰጥ የነበረው ስልጠው
እውቀት፣ ክህሎትና አቅም የሚገነቡ መሆናቸውን በማንሳት ሰልጣኞች በጉብኝቱ ወቅት በተግባር ካዩት ጋር በማቀናጀት ወደ ውጤት ለመቀየር ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በተመሣሣይ የኮንታ ዞን ሰልጣኞችም በዞኑ የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኝተዋል።
ጉብኝቱ ከሰዓት በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሎ እንደሚውል የዘገባው የየዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።
በጌታሁን ግርማ
