የአፍሪካ መሪዎች በአዲስ አበባ – ከውኃ ዋስትና እስከ አዲሱ ትውልድ የፖለቲካ ተሳትፎ

Spread the love

መዲናዋ አዲስ አበባ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም የ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤን ታስተናግዳለች።

ይህ ጉባኤ በአህጉሪቱ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ “አጀንዳ 2063” መሠረት አስተማማኝ የውኃ እና የንፅህና አቅርቦትን በማረጋገጥ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ ከፍተኛ የአህጉሪቱ መሪዎችም በጉዳዩ ላይ ይመክራሉ።

የቅድመ-ጉባኤ መድረኮች እና የውኃ ዋስትና ከዋናው ጉባኤ ቀደም ብሎ ከየካቲት 3 እስከ 6 ቀን 2018 ዓ.ም የተመድ ልማት ድርጅት (UNDP) ከአፍሪካ ሕብረት ጋር በመተባበር በአፍሪካ ቀንድ የከርሰ ምድር ውኃ አጠቃቀም እና የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ ኢንቨስትመንቶች ላይ ያተኮሩ መድረኮችን ያካሂዳል።

የተቋማት ግንባታ እና የሕዝብ አመኔታ በተመሳሳይ ከናይጄሪያ መንግሥት ጋር በመተባበር በሚዘጋጀው የሚኒስትሮች ፎረም፣ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት እና በፖለቲካዊ ሽግግር ወቅት የሕዝብ አመኔታን በማስጠበቅ ዙሪያ ጥልቅ ውይይት ይደረጋል።

የአዲሱ ትውልድ (Gen-Z) ተሳትፎ የዘንድሮው ጉባኤ ሌላኛው ልዩ ትኩረት ሲሆን አዲሱ ትውልድ በአስተዳደር እና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና ማሳደግ ነው።

ይህ በትውልዶች መካከል የሚደረግ ውይይት፣ የወጣቶች የሲቪክ ተሳትፎ ከተቃውሞ ባለፈ በተቋማዊ አሠራር እና በፖሊሲ ቀረፃ ላይ ዘላቂ ተፅዕኖ እንዲኖረው ለማስቻል ያለመ ነው።

በመድረኩም የተመድ ልማት ድርጅት (UNDP) በፖለቲካዊ ሽግግር እና በወጣቶች መሪነት በሚከናወኑ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ላይ ያዘጋጃቸውን አዳዲስ የጥናት ውጤቶች ይፋ ያደርጋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *