ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይል የመገንባት ውጥን ይዛ እየሰራች ነው – ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ

Spread the love

ኢትዮጵያ በ2022 ዓ.ም ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይል የመገንባት ውጥን ይዛ እየሰራች ነው አሉ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለአካዳሚው ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ሌ/ጄነራል ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ተመራቂዎች ለላቀ ግዳጅና አፈፃፀም ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባችኋል፡፡

ኢትዮጵያ የያዘችውን ከአፍሪካ ቀዳሚ አየር ኃይል የመገንባት ውጥን የሚመጥን ቴክኖሎጂና የሰው ኃይል ማብቃት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ አየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያን ከፍታ የማይፈልጉ ሁለት ጠላቶች መኖራቸውን አንስተው÷ የውጭ ጠላቶች እና የእነሱ ተላላኪዎችና ጉዳይ አስፈፃሚዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህን ጠላቶች በመመከትና አከርካሪያቸውን በመስበርም የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቁርጠኛ ሆኖ እየሰራ ነው ብለዋል።

“እኔ ለሀገሬ መስዕዋት እሆናለሁ” ብላችሁ ወደ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተቀላቀላችሁ ተመራቂዎችና ተሿሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *