የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የባለሙያዎችን ክህሎት በስልጠና መገንባት ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከክልሉ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ (FSRP) ፕሮግራም ጋር በመተባበር የበጋ መስኖ ስንዴ አመራረት ፓኬጅ ላይ ከዞንና ከወረዳ ለተወጣጡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የባለሙያዎችን ክህሎት በስልጠና መገንባት ወሳኝ መሆኑ ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ የግብርና ሥራዎች በተለያዩ ወቅቶች የተከፋፈለ መሆኑንና ይህንንም ወቅቶች በተገቢው መጠቀም ከተቻለ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡

መድረኩ በዋናነት ከዞንና ከወረዳ ለተወጣጡ ባለሙያዎች የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የ2018 ዓ.ም የበጋ መስኖ ስንዴ የአሰልጣኞች ቴክንክ ስልጠና መሆኑንና ስልጠናው በዋናነት በሰብል ምርትና ምርታማነት ማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርግ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ለዚህም ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ አግሮ ኢኮሎጂው የሚፈቅደውን ሰብል በተገቢው ሁኔታ እንዲመረት ማድረግ ዋና ሥራችን ሊሆን ይገባልም ብለዋል፡፡

አቶ አሸናፊ አክለውም ከግብርና ምርትና ምርታማነት አኳያ የሚታዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ አርሶ አደሩን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የድጋፍ ክትትል ስራ ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር በሆኑ በአቶ ታገል ታምሩ የበጋ ስንዴ ምርትና ምርታማነት፣ የሰብል ተስማሚነት ስነምህዳር፣ የሰብል አመራረት ዘዴ ያተኮረ ስልጠና ሰነድ እየቀረበ ሲሆን በክልሉ የበጋ ስንዴ ምርትና ምርታማነት በሚፈለገው ልክ ባይሆንም ከማሳ ሽፋንና ከምርታማት አንፃር ከፍተኛ እድገት እየተመዘገበ ማምጣቱ ገልጿል ፡፡

ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑ ከወጣው መርሃ ግብር መወቅ ተችሏል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *