ከ275 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለዉን የቦንጋ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ያለበትን ደረጃ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ጎበኙ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በቦንጋ ከተማ ግንባታዉ እየተከናወነ የሚገኘዉ የቦንጋ አዳሪ ትምህርት የሥራ እንቅስቃሴ ያለበት ደረጃ ምልከታ አድርገዋል።

የቦንጋ አዳሪ ትምህርት ቤት ከ275 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሰዎች ለሰዎች መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ገንዘብ ድጋፍ ግንባታው እየተከናወነ ይገኛል።

የትምህርት ቤት ግንባታ አፈጻጸም በ2ዐ18 ዓ.ም ሚያዝያ ወር መጨርሻ አጠናቅቆ ለማስረከብ በቁርጠኝነት እየተሰራ ስለመሆኑ ማወቅ ተችሏል።

የሥራ ተቋራጩ ሥራውን በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ የሚያስችል ሙሉ የኮንስትራክሽን ግብዓትና የሰው ኃይል በበቂ ሁኔታ ይዘው እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎቹ የትምህርት ቤቱ ግንባታ ያለበት ደረጃ ተዘዋውረው በመመልከት በስራ ላይ የሚገኙ የግንባታ ሠራተኞችንም አበረታትተዋል።

በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ጨምሮ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ተሳትፈዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *