የኢትዮጵያ አየር መንገድ አራት አዳዲስ ኤርፖርቶችን በቅርቡ ሊያስመርቅ ነው

Spread the love

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ አራት የሀገር ውስጥ ኤርፖርቶችን እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ያደቻ በኢትዮጵያ የመሠረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሳምንት መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤በአሁኑ ወቅት በሀገር ውስጥ 23 ኤርፖርቶች አገልግሎት እየሰጡ የሚገኝ ሲሆን፤አራት ተጨማሪ ኤርፖርቶች በቅርቡ ይመረቃሉ፡፡

እነዚህም ነጌሌ ቦረና፤ ሚዛን አማን፤ ጎሬ መቱ እና ደብረ ማርቆስ ኤርፖርት መሆናቸውን ጠቅሰው፤ አየር መንገዱ ቀጣይነት ባለው መልኩ የማስፋፊያ ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሰረት አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ አገልግሎቱን ወደ 27 ኤርፖርቶች ከፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

እ.አ.አ. በ2024 የሀገር ውስጥ አገልግሎቱንና የኤርፖርቶችን ቁጥር 47 ለማድረስ መታቀዱን አስታውሰው፤ አየር መንገዱ ለትርፍ ብቻ ሳይሆን ዜጎችን የማገልገል ዓላማ ይዞ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *