የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ የሌማት ትሩፋትና የኢንዱስትሪ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ

Spread the love

ከመስከረም 04 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ “የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሃሳብ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።

የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስጀመሩት የስልጠና መድረክም የፓርቲው አመራር ሀገራዊ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ የቀጣይ ተልዕኮን በብቃት መወጣት የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

የስልጠናው ተሳታፊዎችም በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን እና አዳማ ከተማ የሌማት ትሩፋትና የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የምርታማነትን አቅምን ለማጎልበት እንዲሁም የስራ ዕድል ተጠቃሚነትን ለማስፋት የተከናወኑ ስኬታማ ስራዎችን ተመልክተናል ብለዋል።

በተለይም በዶሮ እርባታና እንቁላል፣ በወተት ምርትና በዓሳማ እርባታ እንዲሁም በፓፓዬ እና አቮካዶ የፍራፍሬ ምርታማነት ላይ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ ያስቻሉ ተጨባጭ ውጤቶች እንዳሉ አረጋግጠናል ብለዋል።

በመሆኑም በሌማት ትሩፋት እና በአምራች ኢንዱስትሪ መስክ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስፋት ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የጋራ ጥረታችን ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *