የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

Spread the love

በጉባኤውም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር የመንግስታቸውን የ2018 በጀት ዓመት የ6ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

ከቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት መነሻ የክልሉ ምክር ቤት አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶች አንስተዋል።

በዚህም መሠረት

👉የክልሉ መንግስት የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ በወሰደዉ አቋም ከምክር ቤቱ አባላት ሲነሱ ለነበሩ ጥያቄዎችን እየመለሰ እንደሚገኝ ለዚህም አድናቆትና ምስጋና አቅርበዋል።

👉የክልሉ ተቋማት የተደራጀ ድጋፍና ክትትል በማድረግ በየጊዜዉ የተሻለ አፈጻጸም እየተመዘገበ መሆኑን ጠቅሰዋል።

👉የደካ ሳይለም መንገድ ጥገና ጉዳይ እየተጓተተ ስለመሆኑ።

👉ከመሠረተ ልማት አኳያ የዲሪ-ማሻ አስፋልት መንገድ ሥራዉ የተቋረጠ በመሆኑ ዳግም እንዲጀምር ምን እየተሰራ ነዉ

👉 የቦንጋ ከተማ የተበላሸዉ የመሀል አስፓልት ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጡ

👉 የአዲያ–ካካ–ቦንጋ የመንገድ ጥገና ሥራ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ፣

👉 የካካ–አመያ የኮቾ ወንዝ ድልድይ ፕሮጀክት በተያዘው ጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቁ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እያስነሳ በመሆኑ ሥራው ምን ደረጃ ላይ ይገኛል፣

👉 በከተሞች ፊትለፊት የሚከናወነው የኮሪደር ልማት ሥራ አበረታች ቢሆንም በከተሞች ውስጥ ለውስጥ ዝቅተኛ መነቃቃት ያለው በመሆኑ ቀጣይ ምን እርምጃዎች ይወሰዳሉ፣

👉 በምዕራብ ኦሞ ዞን በማዕድን ዘርፍ በኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ወጣቶች ወደ ተግባራዊ ሥራ ለመግባት የሚገጥሟቸው ችግሮች እንዲፈቱ መንግስት ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ፤

👉 በምዕራብ ኦሞ ዞን ሰላምና ጸጥታ ሥራዎች እንዲጠናከሩ በወሰን አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ቀጣይ በትኩረት እንዲሰራ፣

👉በክልሉ በገጠር አከባቢዎች የሚስተዋሉ የመብራት ተደራሽነት እንዲሁም በከተሞች የሚያጋጥሙ የመብራት ኃይል የመቆራረጥ ችግር ለመፍታት መንግስት ምን እርምጃዎችን እየወሰደ ነው፣

👉በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች የክልል ተቋማት ህንጻ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ ተቀምጠው ወደ ሥራ ቢገባም በአንዳንድ ከተሞች የሚስተዋሉ የዝቅተኛ አፈጻጸም መሻሻል እንዳለበት ፣

👉ከደመወዝ ጭማሪ ጋር በተያያዘ በፍጆታ እቃዎች የዋጋ ጭማሪ በየጊዜው እየጨመረ በመሆኑ መንግሥት በዚህ ላይ ምን እየሰራ ነው እየወሰደ ያለው እርምጃ እንዴት ይገለጻል

👉ኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ሰንበት ገበያ ቢቋቋምም የፍጆታ ምርቶች በጥራት፣ በብዛትና በዘላቂነት ከማቅረብ አኳያ ውስንነት ስለሚታይ ይህን ከማሻሻል አንጻር ምን ዕቅድ ተይዟል፣

ከላይ ከምክር ቤቱ አባላት የተነሱ ጥያቄዎች መነሻ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የሚመለከታቸዉ የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *