




የማጃንግ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት መቀበያ በዓል “ዲንከ” በየዓመቱ ወርሃ ጥር መጀመሪያ ሳምንት እንደሚከበርም ታዉቋል
በሲምፖዚየሙ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት
የደቡብ ምዕራብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ደነቀ ማሞ የማጃንግ ብሔረሰብ ውብና ድንቅ ባህል ያለው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ከሰውም ከተፈጥሮም ጋር ተግባብቶ የሚኖር ህዝብ ነው ብለዋል።
ለረዥም ጊዜ የተዘነጋውና የሀገራችን ህገ መንግስት ያጎናጸፈልን በራስ ባህል፣ ቋንቋና እሴቶች መልማት በለውጡ መንግስት ወደ ፊት እየመጣ በመሆኑ የብሔረሰቡን አወንታዊ እሴቶች ለሀገረ መንግስት ግንባታ ማዋል ይጠበቃል ብለዋል።
ይህ ውብ ባህል አድጎና ለምተው ለሠላምና ልማት ግንባታ እንዲውል የክልሉ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል ብለው ክልሉ የሚታወቅበትን አብሮ የመኖር እሴት እያሰፋን የወል ትርክትን መገንባት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ሀገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ተደምረውና ተካባብሮ የሚኖርባት ጥንታዊት ሀገር ሲትሆን ሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ደግሞ የዚሁ ነፀብራቅ ናት ብለዋል።
ማጃንግ ብሔረሰብ ለዘመናት ጠብቆ ያቆዩትን ባህላዊ የግጭት አፈታትና ደን አጠባበቅ ልማዳቸው በጥናት ተደግፈው ለሀገር ጥቅም እንዲውል ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
ይህ ሲምፖዚየም ወንድማማችነትን የሚያጠናክር ልዩ ኹነት ነው ያሉት የጋምቤላ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሽኔ አስቲን በሁለቱ ክልል የሚገኙ የማጃንግ ብሔረሰቦች ባህልና እሴት በማሳደግ ለጋራ ልማትና ቱሪዝም ሀብት ሊናውል ይገባል ብለዋል።
ለበርካታ ዘመናት የተዘነጋው የማጃንግ ባህል ዛሬ ትንሳኤውን አግኝተው እንዲያንሰራራ ያደረገውን የለውጡ መንግስት ትሩፋት እያሰፋን ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ታለመላት ልዕልናዋ የምናደርስበት መንገድ እንደሆነ ገልፀዋል።
የብሔረሰቡን ዘመን አቆጣጠርና አዲስ ዘመን መቀበያ ዕለትን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጠጡት የማጃንግ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዮናስ አበበ የዳበረ ባህልና ያልተበረዘ ቋንቋ ለትውልድ የሚናስተላልፍበት ምዕራፍ ላይ እንደደረሱ ተናግረዋል።
የማህበረሰቡን ማንነትና በህል የሚገልጽ ሙዚየምና በማደራጀት ሁሉን አቀፍ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ በየዓመቱ ወርሃ ጥር በገባ የመጀመሪያ ሳምንት የሚከከረው የማጀሰንግ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት በዓል “ዲንከ” ተብለው እንደሚጠራ አብስረዋል።
የዓመት በዓል ብስራትን ተከትለው የብሔረሰቡ አባቶች ምርቃት አድርገው ሲምፖዚየሙ ማጠቃለያውን አግኝተዋል።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
