የክልሉ ስፖርት ልዑካን ቡድን በአገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ላይ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገቡ እንደሚገኝ ተገለፀ

Spread the love

‎በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር ላይ እየተሳተፈ ያለው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስፖርት ልዑካን ቡድኑ በተለያዩ ስፖርት አይነቶች አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገቡ እንደሚገኝ የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገልጿል፡፡

የቢሮው የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በየነ ቴቃ የዘንድሮ ውድድሩ ለየት ያለ ገጽታ መኖሩን ገልፀዋል።

‎ አቶ በየነ አክለውም መንግስት በታዳጊዎች ላይ በመስራት ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የወሰደው እርምጃ ለነገው የስፖርት ስኬት መሠረት መጣል ነው ሲሉም አብራርተዋል።

‎ታዳጊ ስፖርተኞች ስነሳ አብረው በዋናነት የሚነሳው የዕድሜ ጉዳይ ልዩ ነጥብ እንደሆነ የጠቀሱት አቶ በየነ ቴቃ በዘንድሮ ውድድር እንደሀገር ብሎም እንደክልል ልዩ ትኩረት በዕድሜ ዙሪያ መሰጠት መቻሉንም አክለው ገልፀዋል።

‎ ክልሉን የወከሉ የስፖርት ልዑካን ቡድኖች እስካሁን ያሳየው ስፖርታዊ ጨዋነት ለውጤትና ለአሸናፊነት ምቹ መደላደል እየፈጠረ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

‎በውድድሩ የክልሉ ስፖርት ልዑካኖች በእግር ኳስ፣ በወርልድ ቴኳንዶ፣ በፓራሊምፒክ፣ በብስክሌት፣ በጂምናስቲክ፣ በውሃ ዋና፣ በጤረጰዛ ቴኒስ እና በአትሌቲክስ ውድድሮች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ በየነ በውድድሩም ልዑካኖቹ አበረታች ውጤቶች እያስመዘገቡ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

‎እስካሁን በተደረገው ውድድር የተለያዩ ውጤቶች ተመዝግቧል ያሉት አቶ በየነ ‎ፍፃሜ ባገኘው በጂምናስቲክ ስፖርት ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ሦስተኛነት ደረጃ በመያዝ የነሐሰ ሜዳልያ ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

‎በፓራ-ሊምፒክ ውድድር በሴቶች በአይን ጉዳት አትሌቲክስ ውድድር ነሐስ ሜዳልያ፣ እጅ ጉዳት 100 ሜትር በወንዶች ነሐስ ሜዳልያ፣ በእግር ጉዳት ክላስ – ቢ በሴቶች አሎሎ ውርወራ ብር ሜዳልያ፣በወንድ እጅ ጉዳት ጦር ውርወራ የነሐስ ሜዳልያ እና በሴት እግር ጉዳት ጦር ውርወራ የብር ሜዳልያ ማስመዝገበ የተቻለ መሆኑ ተገልጿል።

‎በቡድን ሴቶች የወለል ተግባር ሌጣ ፈረስ 3ኛ ደረጃ በመያዝ መጠናቀቅ የቻለው ሲሆን ‎በወንዶች የወለል ተግባር ሌጣ ፈረስና የትይዩ ጥንድ አግዳሚ በተመሳሳይ አዲስ አበባ ከተማ፣ አማራ ብሔራዊ ክልል እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልሎች በመሆን አሸንፈዋል።

‎በእግር ኳስ ውድድር ከምድብ አንደኛ በመሆን ስድስት ጎል እና ስድስት ነጥብ በመያዝ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፋቸውም የተረጋገጠ ሲሆን ለዋንጫው ለማለፍ ነገ 8:00 ከአቻቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋር ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውንም አቶ በየነ ጠቅሰው ለቡድኑ ውጤት መልካም ምኞታቸውን ተገልጿል።

በተከተል ወ/ ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *