








ሴቶች ሀገረ መንግስት በመገንባት ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና አጠናክረው ሊወጡ ይገባል ሲሉ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቦንጋ ማዕከል ክልል ተቋማት የሴቶች ሊግ መሰረታዊ ድርጅት የአንደኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል መሪ ሀሳብ የመሰረታዊ ድርጅት አባላት ከውይይተ ጎን ለጎን ብልጽግና ፓርቲ የተመሠረተበትን 5ኛ አመት አክብረዋል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ አቶ ነጋ አበራ እንደገለጹት የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በየደረጃው ያሉ የሴቶች አደረጃጀቶችን በማጠናከር በትብብር መስራት ይጠበቃል ሲሉ አስገንዘበዋል ።
በሴቶች በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳለቸው የገለጹት አቶ ነጋ ይህንን ተሳትፎአቸውን በማሳደግ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት የተቀናጀና የተደራጀ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።
ሴቶችን በማብቃትና ወደ ውሳኔ ሰጭነት በማምጣት ፓርቲያችን ብልጽግና በልዩ ትኩረት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን የፓርቲያችን እሳቤዎች ወደፊት ለማሻገር በቁርጠኝነት መስራት እንዳለበት ገልጸዋል።
ብልጽግና የህዝባችንን ፍላጎት ከዳር እንዲደርስ ታሪካዊ ሀላፊነት በመዉሰድ ባለፉት አምስት ዓመታት ተስፋን የጫሩና ህዝባችንን ያነቃቁ ስኬታማ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል።
ሁለንተናዊ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ ቀን ከሌት የሚተጋው ፓርቲያችን በርካታ ታሪካዊ ስብራቶችን እየጠገነ ሀገራችንን በፅኑ የህብረብሔራዊ አንድነት መሰረት ላይ እየገነባ ይገኛል ብለዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ወ/ሮ ውባለም በዛብህ እንደገለጹት በሊጉ መሪነት የሴቶችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል ።
የሴቶችን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለተአፈጻጸምም ካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ሴቶች የግንባር ቀደምነት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠቅሰዋል።
በቀጣይም የሊጉን አባላትን በተደረጀ ሁኔታ በመፈጸም የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የሊጉ መሰረታዊ ድርጅት አመራር በሆኑት በወ/ሮ ጌጤነሽ ገበየሁ 1ኛሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በመጨረሻም በተጓደሉት የመሠረታዊ ድርጅት አመራሮች ሟሟያ የተደረገ ሲሆን የኢንስፔክሽን ኮሚቴ አባለት ምርጫ ተካሂዷል።
