
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ፤ ብልጽግና ፓርቲ በአንደኛው መደበኛ ጉባኤ ካስቀመጣቸው ውሳኔዎች እና ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የፓርቲው ተግባራትን አስመልክቶ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ ነጋ አበራ በጋዜጣዊ መግለጫቸውም ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በፖለቲካው ዘርፍ በርካታ ዘርፍ ብዙ ተግባራት ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በመሠረቱ እንደ አንድ ፓርቲ ሲመሰራት የለውጥ ፍላጎት ያላቸው የቀድሞ ፓርቲ አባላት እና ህዝቡ ውጫዊ ሃይል በፈጠረው ግፍት የተፈጠረ ታላቅ ፓርት ነው ብለዋል በመግለጫቸው፡፡
በመጀመሪያዉ የፓርቲው ስፈጠር እንደ ሀገር በርካታ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች የነበረበትን ይዞ የተነሳው ፓርቲ ነው ብለዋል።
በወቅቱ ከነበረው ስብራቶች አንዱና ትልቁ ስብራት የፖለቲካ ስብራት መሆኑንና ለሌሎች ስብራቶች እንደ መነሻ ተደርጎ ሲወሰድ አንደነበረም ተናግረዋል።
ከዚህም አንፃር በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት የነበሩ የፖለቲካ ባህልና አስተሳሰቦች አንዱ ሌላውን የሚታገልበት መንገድ ዴሞክራሲያዊ ሳይሆን በጠመንጃና በጉልበት የምያሻንፍበት እና ወደ ፊት እንዲቀጥል የመፈለግ አስተሳሰቦች የነበሩበት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ይህንን ባህል መቀየር ለብልፅግና ፓርቲ አንዱ ትልቅ ስራ ነበር፣ የጽፈኝነት አስተሳሰቦች በሀገራችን ሰፊ ቦታ ነበራቸው ለዚህም በሀገሪቱ በርካታ የተለያዩ ባህል፣ ቋንቋና ታርክ የሚንጸባረቅበት በመሆኑ ይህንን በአግባቡ ማስተናገድ የሚችል የፖለቲካ ስርዓት በማስፈለጉ ይህንን ለመወጣት በብልጽግና ፓርቲ በመጀመሪያ ጉባኤው ከተቀመጠው ውሳኔ መነሻ ከዚህ በፊ በኢትዮጵያ ውስጥ ባልተለመደ መልኩ አዲስ የፖለቲካ ባህል ይዞ በማምጣት በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በዚህም መነሻ ከዚህ በፊት ይዘን የመጠናቸውን የፖለቲካ ባህልና አስተሳሰብ በማስቀረት ከዚህ ቀደሙ ጋር አሁን ያለውን አቅም አዳምሮ ለነገ የተሻለ ለመስራት አዲስ የሪፎርም አስተሳሰብ ይዞ መምጣቱን ነው አቶ ነጋ አበራ የጠቆሙት።
ከሪፎርም አንዱ የመደመር እሳቤ የብልጽግና ፓርቲ ትልቁ እሳቤ ተደርጎ የሚወሰደው መሆኑን አንስተው የመደመር እሳቤ መነሻውም መደረሻውም ብልጽግና እንደሆነም አብራርተዋል።
በዚህም ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች መስራቱንና ይህንን ለማሳካት በ3 አንኳር ጉዳዮች በሰብዓዊ ልዕልና፣ኢኮኖሚያዊ ልዕልና እና በአፍሪካ ውስጥ በፖለቲካው ሀያል ሀገር የመገንባት ትልሞች ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ መሆኑን አቶ አቶ ነጋ አንስተዋል።
ክልሉ በፖለቲካ ዘርፍ የነበሩ ስብራቶችን በመፍታት ሁለንተናዊ ብልጽግና ለመረጋገጥ የመደመር አስተሳሰቦችን ተግባራዊ በማድረግ ትብብር ማዕከል ያደረጉ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባትን መነሻ ያደረጉ ተግባራት በመሰራተቸው በርካታ ለውጦች መጥቷል ነው ያሉት አቶ ነጋ አበራ።
በክልሉ ዉስጥ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለመገንባት ከዚህ ቀደም የነበረውን በተለያዩ ግንዛቤ እጥረት የሚያለያዩ አስተሳሰብና አመለካከት ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገው ተከታታይ ውይይቶች ወደ አንድ ወደሚያደርጉ ሀገራዊ አስተሳሰብን የመፍጠር ትርክት መገንባት መቻሉን ጠቁመዋል።
ከኢኮኖሚው አንፃርም በሀገራችን የተለያዩ አስተሳሰብና አመለካከት የነበረበት በመሆኑ ባለፉት ሶስት ዓመት በተፈጠረው ብልፅግና ፓርቲ ምቹ ምህዳር የብዙሃ ኢኮኖሚ መገንባት የሚያስችሉ አስተሳሰቦች መፍጠር በማስፈለጉ በ5 ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ መሠረት በማድረግ በተሰራው ስራ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ክልሉ በማህበራዊ መስክም ብልጽግና ሰው ተኮር ፓርቲ በመሆኑ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት በፓርቲው እንሼቲቪ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የፓርቲው ስራዎችን ለማሳካት ጠንካራ ፓርቲ መገንባት ለተቋምና ለሀገር ግንባታ ጉልህ ድርሻ ያለው በመሆኑ ለዚህም የፓርቲ አመራር እና አባል አቅም ለመገንባት በርካታ ሀገራዊ እና ክልላዊ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ተሰጥቷል ብለዋል።
ከ600ሺህ በላይ የክልሉ አመራር እና አባል ተሳታፊ ሆኖ በክልሉ በፖለቲካው መስክ በርካታ መነቃቃት ተፈጥሯል ስሉም አክለዋል፡፡
አቶ ነጋ አበራ አክለውም ጠንካራ ፓርቲ አባልና አመራር የመገንባት ጉዳይ ቀጣይ ትኩረት የሚሰጥ ጉዳይ ይሆናል ነው ያሉት ።
ከሁለተኛው ብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ በኋላ የአመራር እና የአባላት ግንዛቤ የተፈጠረ እና በክልሉ የሚገኙ 540 ሺህ በላይ የፓርቲው አባላት እንዳሉና ጠንካራ አመራርና አባል ለመገንባት አባላቱንና አመራሩን የመመዘን እና የአስተሳሰብ ዝንፈት ያለባቸውን አባልና አመራርን የማጥራት ስራ መስራቱን ተናግረዋል። በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ነጋ አበራ በመጨረሻም መላው የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አባልና አመራር የፓርቲው ደጋፊዎች ባለፉት ጊዜያት በፖለቲካው መስክ ላደረገው ተሳትፎ አመስግነው አሁንም መላው የክልሉ ፓርቲ አባላት በክልሉ ለሚደረገው ሁሉ አቀፍ የፓርቲው ተግባራት ላይ የሚያሳየውን ሁለንታናዊ የፓርቲ ድጋፋቸውን አጠናክሮ በማስቀጠል በብልጽግና ፓርቲ ጎን እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
