jgjjh

Spread the love

የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ “ከቃል እስከ ባህል”በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ የውሳኔ አቅጣጫዎች ላይ “የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሚና” በሚል መሪ ቃል ውይይት በቦንጋ ከተማ አካሂዷል።

ለውይይት የተዘጋጀውን ሰነድ የፌዴራል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክር ቤት አባልና የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ስራ-አስፈፃሚ ወጣት ፈቀደ አለሙ አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል።

ወጣቶች የሀገር ግንባታ ላይ የዜግነት ድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን በመድረኩ ላይ ተገኝተው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌ ገልጸዋል።

በዞናችን ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል ያሉት አቶ አጥናፉ ኃይሌ በተያዘው በጀት ዓመት ብቻ ከ15 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች በቋሚና ጊዜያዊ ስራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

በሀገር ግንባታ ላይ ትውልዱ መቻቻልን፣ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ፣ወንድማማችነትና እህታማማችነትን እንዲሁም አርበኝነትን እየተማሩ እንዲያድጉ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ኃላፊው ተናግረዋል።

የሚዲያ ነጻነትና ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ አፍራሽ ተልዕኮ ይዘው ሚዲያውን ለግጭት፣ ለብጥብጥና ለሁከት ብሎም ባልተገባ መንገድ የግል ጥቅም ለማስጠበቅ ካላቸው የተሳሳተ ፍላጎት በሚጠቀሙት አካላት ላይ ህግ የማስከበር ሥራ ይሠራል ብለዋል።

የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት መላውን ሕዝብ በማሳተፍ ማህበራዊ ሚዲያውን ለገዥ ትርክት ግንባታ፣ለህብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ለዕውቀት ሽግግር እና የኢትዮጵያን እውነት ለመግለጥ እንዲጠቀሙበት የማድረግ ሥራ እንደምሰራ አስረድተዋል።

የስነ-ምግባር ችግር ያለባቸውን የፓርቲውን አመራርና አባላት በትግል በማጥራት እርምጃ የመውሰድ እና የምዘና ስርዓት መዘርጋት ስራ አጽንኦት ተሰጥቶ እንደምሰራ ጠቁመዋል።

ፓርቲያችን ያስቀመጠው አቅጣጫ ውጤታማ እንዲሆን የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ጎልቶ እንዲወጣ ግንባር ቀደም አመራሮችና የክንፉን አባላት በማወያየት ለተፈጻሚነቱ እንዲተጉ ማድረግ እንደምገባ የካፋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ህዝብ ግንኙት ዘርፍ ኃላፊው አቶ ታከለ ታምሩ ገልጸዋል።

ወጣቶች የገዥ ትርክት ግንባታ ማጠናከር ፣ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን እንዲጠናከር ማድረግና የሠላም ግንባታ ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆን አለባችሁም ብለዋል አቶ ታከለ።

የብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸውን ውሳኔ አቅጣጫዎችን ውጤታማ ለማድረግ የፓርቲው አመራርና አባላት ብቃትና ጥራት ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደምሰራም አስረድተዋል ።

የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ወጣት ወንዱ መንገሻ በበኩሉ የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ ኃላፊነት የተጣለው ወጣት መሆኑን ተናግረዋል።

የመላው ክልላችን ወጣቶች ለሀገር ልማት፣ለሠላም ግንባታ፣ለህብረ ብሔራዊ አንድነትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበረከት አለባችሁ ብለዋል።

የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት መንግሥቱ በየነ እንዳሉት በሁሉም መስክ የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ አቅጣጫ ላይ የተቀመጡ ውሳኔዎችና ሀሳቦች ለወጣቱ ለማስረጽ ዓላማ ያደረገ ውይይት እንደሆነ ተናግረዋል።

ወጣቶች በሀገራችን ውስጥ ለውጡ እንዲመጣ ያደረጉት የፖለቲካ ትግል አሁን ላለንበት የማንሰራራት ምዕራፍ ላይ ትልቅ ሚና እንዳለው ፓርቲያችን ያምናል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የፖለቲካ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ገፅታ ያለው ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

በዞናችን ከፖለቲካ ተሳትፎ አንጻር ካሉን 6 መቶ 45 አመራር ውስጥ የወጣቶች የፖለቲካ ተሳትፎ 48% የደረሰ ሲሆን አሁንም ቢሆን ትኩረት ሰጥተው መስራትን ይጠይቃል ብለዋል።

የውይይት ተሳታፊዎች በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ በርካታ ጥያቄዎችና ሀሳቦች ያነሱ ሲሆን መድረኩን በመሩት አካላት ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

በመጨረሻም የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አጥናፉ ኃይሌን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲ ወጣት ክንፍ አመራሮችና አባላት የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂዷል ሲል የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *