የዞኑን አቅም በአግባቡ የለየ ሥራ መስራት እንዲሁም ለዉጥ የሚያመጣ ድጋፍና ግምገማን ስርዓት ፈጥሮ መምራት ይገባል:-አቶ የሺዋስ ዓለሙ

Spread the love

የክልሉ ድጋፍና ክትትል ቡድን በዞኑ ያሉትን ወረዳዎች፣ከተማ አስተዳደሩን እና ቀበሌዎችን በመንግስትና በፓርቲ የተሰሩትን ሥራዎች ዙሪያ ለዞን አመራሮች ግብረ መልስ ሰጥቷል

በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ያለበት ደረጃ በተጨባጭ ወርዶ በማረጋገጥ በሶስት ወረዳ እና በአንድ ከተማ አስተዳደር ዞን መዋቅርን ጨምሮ ምልከታ በማድረግ ለዞኑ አመራር ግብረ መልስ ተሰጥቷል።

የድጋፉ ዋና ዓላማ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን መድረክ ላይ ከመገምገም ባለፈ መሬት ላይ ያለበትን ደረጃ ምልከታ በማድረግ ጥንካሬና ጉድለቶችን በመለየት ፣ጉድለቶች በማረም በጥንካሬ የተመዘገቡትን በማስቀጠል በቀጣይነት እንደሚሰራም አቶ የሺዋስ ዓለሙ ጠቅሰዋል።

በዚህ ከዞን ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ በመዉረድ ዝርዝር ስራዎችን ማየት መቻሉን ጠቅሰዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ አለሙ ግብረ መልሱ ላይ በበበጋ መስኖ፣የሙዝ ልማት፣ በቡና እየተጀመሩ ልማት፣በእንስት፣ በዶሮ መንደር እንዲሁም በትምህርት የተማሪዎች ምገባ በአዳሪ ትምህርት ጉዳይና በተማሪ ውጤት ማሻሻያ የተጀመሩ ሥራዎች እንዲጠናከሩ ግብረ መልስ ሪፖርት አቅርበዋል።

ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት መዘርጋት፣አቅም ያለዉ ግንባታና ፖለቲካ የስራ መስራት፣በገቢ አፈጻጸም፣ የከተማ ኮሪደር መዘግየት፣የገጠር ኮሪደር አለመጀመር፣የተቀናጀ የፖለቲካ ስራ፣የሌማት ትሩፋት ሥራ፣የሰንበት ገበያ ፣የኢንቨስትመንት አፈጻጸም ለማሻሻል በተለየ ፍጥነት እና ስርዓት መመራት እንዳለበት በግብረ መልስ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ ዞኑ ላይ ቀጣይነት ያለዉ ለዉጥ

እንዲ መጣ የዞኑን አቅም በአግባቡ የለየ ሥራ መስራት እንዲሁም ለዉጥ የሚያመጣ ድጋፍና ግምገማን ስርዓት ፈጥሮ መምራት ይገባል ብለዋል አቶ የሺዋስ።

የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ እንደ ዳውሮ የፓርቲ አባላትን ከማፍራት፣ ውይይት ከማድረግ አኳያ አጠቃላይ በፓርቲ ሥራዎች አጠናክረን መሥራት እንደሚገባ በመጠቆም እንደ መንግስት በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርትና በከተማ እና ገጠር ኮሪደር ስራዎች በማጠናከር ጉድለቶችን ቶሎ ማረም እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ የክልሉ ቡድን አመራሮች በዞናችን በቆዩባቸው ጊዜ ጠንካራ ምልከታ ማድረጋቸውን በማመስገን ቀጣይነት ያለዉን የድጋፍ፣ክትትልና የግምገማ ስርዓት በቀጣይነት ልሰራ እንደሚገባ አንስተዋል።

አቶ ታርኩ ይህ የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ተግባራትን ባህል በማድረግ አሁን በግብረ መልሱ የተነሱትን ነጥቦችን ለቅመን በመውሰድ ጥንካረዎችን በማስቀጠል ድክመቶችን ቶሎ ማረም እንደሚገባም ገልፀዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *