ለሀገራዊ ብልጽግና ጉዞ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

በምዕራብ ኦሞ ዞን የብልጽግና ጉዞ፣ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያ ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫ በሚል የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት እየተመዘገበ ላለው ስኬትና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ እያበረከተው ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የዞኑን ማህበረሰብ ያማከለ የሚዲያ አውታር እንዲመሰረት፣ አጫጭር ስልጠናዎችና ድጋፍና ክትትል ቢደረግ፣ ዘርፉ ትኩረት የሚፈልግ በመሆኑ በየደረጃው ትኩረት እንዲሰጠው፣ የሚዲያ ተደራሽነቱን ለማሳደግ የኔትወርክ ችግር ቢቀረፍ የሚሉ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የምዕራብ ኦሞ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጌልታ፦ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን በመንግስት እና በህዝብ መካከል ደልድይ ሆኖ ህዝብን ከመንግስት የሚያገናኝ መሆኑን ጠቅሰው ባለፉት ዓመታት የሀገራችን የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።

አቶ ደሳለኝ አያይዘውም ሚዲያን በአግባቡ ከተጠቀምንበት ሀገር የሚገነባ በመሆኑ በአግባቡ መጠቀም ተገቢ መሆኑን ተናግረው በዞኑ በሚገኙ የቱሪዝም ሀብቶችና ቀጣይ ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራት ይገባል ብለዋል።

ሀሰተኛ የፌክ ቡክ አካውንት በመክፈት ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ አካላትን መታገል እንደሚገባ የተናገሩት አቶ ደሳለኝ ወቅታዊ የህዝብ አስተያየት መሰብሰብ ለሚመለከተው አካል ማድረስ በቀጣይ ትኩረት የተሰጠው ተግባር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።

የምዕራብ ኦሞ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አቤል ኢሳያስ፦ በመጣንብት ሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው በቀጣይ ሀገራዊ አውዱን በመገንዘብ ወቅቱን ሊመጥን የሚችል ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።

አቶ አቤል ሀ መንግስት ምን እየሰራ እንደሆነ ለህዝቡ ትክክለኛውን መረጃ ማድረስ ይገባል ማለታቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *