ፊቼ ጫምበላላ በዓል በሶሬሳ ጉዱማሌ እየተከበረ ነው

Spread the love

የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ የሆነው ፊቼ ጫምበላላ በዓል በሶሬሳ ጉዱማሌ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ደስታ ሌዳሞ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ፣ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሣን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሀገር ሽማግዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የበዓሉ እንግዶች እየታደሙ ነው።

የአከባቢው ማኅበረሰብ እና ከሌሎች ስፍራዎች በዓሉን ለመታደም የተሰበሰቡ እንግዶች የሲዳማን አዲስ ዓመትን ለመቀበል እና ለማክበር በቦታው ተገኝተዋል።

ታዳሚዎቹ ጭፈራዎች እና ትርኢቶችንም እያቀረቡ ሲሆን ለአዲሱ ዓመት (ለፊቼ ጫምባላላ) እንኳን አደረሰን እያሉ መልካም ምኞታቸውን እየገለጹ ነው።

የአከባቢው ነዋሪዎች እና ሽማግሌዎችም ዓመቱ የሰላም እና የልምላሜ እንዲሆን እየመረቁም ይገኛሉ።

ፊቼ ጫምበላላ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ ቅርሶች ተብሎ ከተመዘገበ ዘንድሮ 10ኛ ዓመቱ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *