የወንጀል ምርመራ መዝገብ ውጤታማነት ለማሳደግ የአቅም ግንባታ መጠናከር እንደሚገባ ተጠየቀ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፍትሀ ቢሮ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በወንጀል ምርመራ ውጤታማነትና በቅንጅታዊ ስራዎች ዙሪያ በተዘጋጀው የምክር መድረክ የተገኙ ተሳታፊዎች፣

የወንጀል ምርመራ መዝገብ ውጤታማነት ለማሳደግ የዐቃቤያነ ሕጎች እና የመርማሪ ፖሊሶች የአቅም ግንባታ ስራዎች ትኩረት ተስጥተው መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በወንጀል ምርመራ ሂደት በሠብዓዊ መብት አያያዝ መሻሻል እንዳለበት የጠየቁት ተሳታፊዎቹ፥ በምርምር ሂዴት የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ዘመኑ የደረሰበት የምርምራ ቴክኖሎጂ የተደገፈ መኾን እንደሚገባ አንስተዋል።

የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ማሻሻያ የሚፈልጉ ደንቦች መኖራቸውን የገለጹት አስተያየት ሰጪዎቹ በተላይም የምስክሮች አበል አከፋፈል ደንብ ፈጥኖ መሻሻል እንዳለበት አመልክተዋል።

ለክስ መዝገብ መቋረጥ በተዘባ መልኩ የሚደረጉ ጠልቃ-ገብነት መኖሩን ያነሱት ተሳታፊዎቹ ከዚህም ባሻገር በራሱ በፀጥታ ተቋማት ውስጥ ባልተገባ መልኩ መዝገብ እንዲቋረጥ የማድረግ አዝማሚያ ያለ በመኾኑ ተጠያቂነትን ማስፈን ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ የዘርፉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተት በአቅም ግንባታ በማሳደግ እና የተጠያቂነት አሰራርን በማስፈን የወንጀል ምርመራ መዝገብ ውጤታማነት ማሳደግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የተጀመረው የጋራ ውይይት በየደረጃው መጠናከር እንዳለበት ያነሱት አስተያየት ሰጪዎቹ በቀጣይ የዘርፉን ውጤታማነት በማሳደግ ፍትህን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *