ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ መካሔድ ጀመረ

Spread the love

ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ሥርዓት ጉባኤ የመክፈቻ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ መካሔድ ጀምሯል።

በጉባኤው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ፣ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር መሃመድ አሊ የሱፍ ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ፣ የኮሞሮስ ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒ፣ የላይቤሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄርሚያ ካፓን ኮንግ እንዲሁም የሌሎች ሀገራት መሪዎችና ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ፣ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት(ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩና ሌሎች ከፍተኛ የአለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤው ኢትዮጵያ በምግብ ስርዓት ሽግግርና በምግብ ራስን ለመቻል እያከናወነች ያለው ተግባርና የተመዘገቡ ውጤቶች በተለያየ ሁነት ይቀርባሉ።

በተመሳሳይ ጉባኤው በመጀመሪያው ጉባኤ የተገቡ ቃሎችና የተገኙ ውጤቶችን በመገምገም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘላቂ የምግብ ስርዓትን በአለም ላይ እውን ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች እና ተግዳሮቶች ላይም ምክክር ይደረጋል።

ጉባኤውን ለመዘገብ በርካታ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *