በቤንች ሸኮ ዞን ” ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ጳጉሜ 4 የማንሰራራት ቀን በፓናል ውይይት ተከብሯል።



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጅዋ ሳፒን እንደገለፁት የህዳሴ ግድብ በራስ አቅም ብቻ ተገንብቶ ሲመረቅ ደስታው ልዩ የሚያደርገው ከህፃን እስከ አዋቂ የመላው ህዝባችን አሻራ ያለበት የደምና የላብ ውጤት ነው ብለዋል።
የመንሰራራትን ቀን ስናከብር በቀጣይ ለመስራት ያቀድናቸውን እጅ ለእጅ ተያይዘን ከሰራን ከውጤት እንደምናደርስ የታላቁ ህዳሴ አርአያ የሆነ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
በፓርቲያችን መሪነት አቅደን በምንሰራቸው ሥራዎች የገጠሙንን ፈተናዎች ያለፍንበት ብዙ አስተምሮናል ብለዋል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን እንደገለፁት የማንሰራራት ቀን ጳጉሜ 4 ሲከበር ታላቁ የህዳሴ ግድብ የተመረቀበት የአንዱ ማንሰራራት አመላካች ነው ብለዋል።
አንዱ የጀመረውን አንዱ በተሻለ ሁኔታ በማስቀጠል አንገታችንን ቀና እንድናደርግ ያደረገን የፓርቲያችን ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።
ከሀገር በቀል እሳቤ የመነጨ የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም ኢኒሼቲቭ የአፈፃፀም ውጤቶችን በመገንዘብ ለቀጣይ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ውጤታማነት ተጠቃሚነት ሁሉም የድርሻውን በመወጣት እያንሰራራ መሄድ አለበት ብለዋል።
ሀገራችን የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ልማት በማከናወን ሀገራችን የአለም የሁነት ማዕከል ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ላይ በዞናችን እየተገነባ ያለው የገበታ ለትውልዴ አካል የሆነው የደንቢ ሎጅና ፏፏቴ አንዱ ነው ብለዋል
በኮሪደር ልማት የደቀቁና የተጎሳቆሉ የከተማ ሰፈሮችን መልሶ በማልማት ከተሞች የማንሰራራትና የብልፅግና ተምሳሌት መሆናቸውን የሚያሳይ ሥራ እየተሰራ ነው።
ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ፣ ከተረጂነት በመላቀቅ ፣ በኢኮኖሚ ነፃነትና ተወዳዳሪ መሆን፣ሁሉንም ፀጋዎች በማልማት ማንሰራራትን ማሳየት አለብን ብለዋል።
የክልሉ የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሸብር ኢካሎ የማንሰራራትን ቀን የተመለከተ ሰነድ እያቀረቡ ነው።
እንደ ቤንች ሸኮ ኮሚዩኒኬሽን ዘገባ በመድረኩ የክልል፣ የዞን የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
