የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግርኛ ቃለ-መጠይቅ ዋና ዋና ፍሬ-ሐሳቦች

Spread the love

የሰሜኑ ጦርነት መንስኤዎችን በተመለከተ

✅ ሕወሓት ከ50 ዓመት በፊት በነበረ ኋላቀር አስተሳሰብ የታሰረ መሆኑና ለውጥን ለመቀበል አለመፈለጉ። ዓለም በቴክኖሎጂና በ”ፕራግማቲዝም” በምትመራበት ዘመን፣ ድርጅቱ በአሮጌው መንገድ ለመጓዝ መሞከሩ ለግጭት ዳርጎታል።

✅ ቆሞ ቀሩ ኃይል “ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” የሚል የተሳሳተ ስጋት በመዝራት የለውጡን ኃይል እንደ ጠላት ማየቱ።

✅ በኢትዮጵያ የነበረው የተሳሳተ ትርክት ዜጎች በጥርጣሬ እንዲኖሩ ማድረጉ።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፡-

✅ መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ሰላም እንዲያገኝ ባንክ፣ መብራትና ቴሌኮም የመሳሰሉ አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጸዋል።

✅ ሆኖም ቆሞ ቀሩ ቡድን ስምምነቱን “መርጦ የመተግበር” (Cherry-picking) ዝንባሌ እያሳየ መሆኑን ተችተዋል። በተለይም የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ አለማክበሩን ጠቅሰዋል።

✅ ድርጅቱ ለልማት የተመደበውን በጀት ለጦርነት ዝግጅትና ለታጣቂዎች ቀለብ እየዋለ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም በትግራይ ሕዝብ ላይ ተጨማሪ መከራ እያመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ፡-

✅ ጦርነት ሁልጊዜም አስከፊ ገጽታ እንዳለው ገልጸው፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ (Transitional Justice) አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

✅ ይህ ሂደት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ ሊካሄድ እንደሚገባውና ወንጀል የፈጸሙ አካላት በሕግ መጠየቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የኤርትራ መንግሥት (ሻዕቢያ) ሚና

✅ በጦርነቱ ወቅት የኤርትራ ጦር ያደረገው ድጋፍ የሚታወስ መሆኑን ጠቅሰዋል።

✅ ሆኖም በጦርነቱ ሂደት የተፈጸሙ ማናቸውም ዓይነት ጥፋቶች፣ ግድያዎችና ዘረፋዎች (በተለይም በአክሱም፣ ዓድዋና ሽሬ አካባቢዎች) የማይቀበሉትና የሚወገዝ ተግባር መሆኑን በግልጽ አስታውቀዋል።

✅ መንግሥት ማንኛውንም የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት እንደሚቃወምና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር እንደሚሠራ ገልጸዋል።

የሰላምና የልማት ጥሪ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለትግራይ ሕዝብና ወጣቶች ያስተላለፉት መልዕክት፡-

✅ “የትግራይ ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምና ልማት ይገባዋል” ብለዋል።

✅ ወጣቶች የስልጣን ባለቤት እንዲሆኑና በአሮጌ አስተሳሰብ ለጦርነት ከሚገፋፏቸው አካላት ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል።

✅ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰላም እንዲሰፍንና ዳግም ጦርነት እንዳይከሰት ጽኑ ፍላጎት እንዳለውና ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት እንደሚከፍል አረጋግጠዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *