


“ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል ርዕሰ ለክልል ማዕከል የመንግስት ሠራተኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።
ስልጠናው ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች በመዳሰስ የተመዘገቡ ድሎችንና እየገጠሙ ያሉ ፈተናዎች ፣ የመፍትሔ ሀሳቦች እንዲሁም ቀጣይ የጉዞ የሚያመልክት በተለያየ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተዘጋጀ ነበረ።
ስልጠናው ከመቼውም ጊዜ በላይ የአስተሳሰብ፣የአመለካከትና የተግባር አንድነት በማጠናከር እና አቅም በማጎልበት ወቅታዊ ፈተናዎችን በገዥ ትርክቶች ላይ ተሞርኩዞ በመመልከት ጊዜን በአግባቡ በመምራት ምቹና ቀልጣፋ አግልግሎት ለተገልጋዩ እንዲሰጥ የሚያስችል መሆኑንም የስልጠና ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
አስተያየት የሰጡን የስልጠናው ተሳታፊዎች ነጠላ ትርክቶች መከፋፈልና መገፋፋትን ማዕከል አድርጎ የሚንቀሳቀስ ለሀገራዊ አንድነትና ሀገር መንግሥት ግንባታ የማይጠቅሙ የአንድን ወገን ፍላጎት ብቻ የሚያስጠብቅ በመሆኑ ከዚህ በመላቀቅ በገዥ ትርክቶች ላይ ማተኮር ለሀገራዊ አንድነት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ብሄራዊነት ገዥ ትርክትን መገንባት አስፈላጊ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ስልጠናው በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤን የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።
ሲቪል ሠርቫንቱ በተሰማራበት ሙያ መስክ ህብረብሔራዊ አንድነትን በመከተል ከብሔር፣ ከኃይማኖት ጽንፈኝነት እንዲሁም ከየትኛውም ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ህብረተሰቡን ማገልገል እንዳለባቸውም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ከትናንት ወረቶች የሚጠቅሙንን በመውሰድና መጥፎውን በመተው ለነገ የተሻለ ሀገር ለመገንባት በአማካይ እይታ ላይ መቆምና የጋራ ማንነቶችን ማጉላት ይገባል ያሉት ሰልጠኞቹ ያገኙት ስልጠና የግል ህይወትን ጭምር በአዎንታ ለመምራት የሚያስችላቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
በዕድገቱ በዛብህ
