ድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ 527 ሺህ 954 ህጻናት በተቀናጀ መልኩ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ክልል የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ከግንቦት 6-15/ 2017 ዓ/ም ባለው ጊዜ እንደሚካሄድ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል ።

በክልሉ ዕድሚያቸው ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ 527 ሺህ 954 ህጻናት በተቀናጀ መልኩ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጣቸው የክልሉ ጤና ቢሮ በላከልን መረጃ ገልጿል ፡፡

ለኩፍኝ ክትባት ዘመቻ የቅድመ ዝግጅት ሰራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን የገለጸዉ ቢሮ ለዚህም የባለሙያዎች ስልጠና ፤ የክትባት እና ሌሎች ግብዓቶችን በሁሉም ዞኖች የማዳረስ ስራ የተሰራ ሲሆን በቀሪ ቀናት ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ በተያዘለት ሀገር አቀፍ የዘመቻ ቀናት በሁሉም ዞኖች እና ወረዳዎች ዘመቻውን በተሳካ መልኩ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን ጠቅሷል ፡፡

ከኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻው ጎን ለጎን ሌሎች በቅንጅት የሚሰሩ የህጻናት እና የእናቶችን ጤና የሚያጠናክሩ ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን የመደበኛ ክትባት ስራዎችን የማጠናከር ስራ ተጠናክሮም ይሰራል ብለዋል ።

ዕድሜያቸው ከ2-5 ዓመት የሆኗቸው ፣ መደበኛ ክትባትን ፈጽሞ ሳያገኙ የቀሩ እና ያቋረጡ ህጻናትን ለይቶ የመከተብ ፣ለህጻናት ፣ለነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች የስርዐተ ምግብ ልየታ የማድረግ እና የፊሰቱላ ልየታ በመስራት ወደ ህክምና መላክ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆኑ የጤና ቢሮ አመልክቷል ።

ከዚህም ጎን ለጎን የCOVID 19 መከላከያ ክትባት ለሚመለከታቸው የማዳረስ ስራ ተጠናክሮ የሚሰራ ይሆናል ስልም ብሎ አመልክቷል ።

የታመሙ ህጻናትን የመለየት እና ህክምና እንዲያገኙ ወደ ጤና ተቋማት መላክ እንዲሁም በተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ የክትባት ዘመቻ ወቅት ሁሉም ታላሚ የተደረጉ ህጻናት እና ሌሎች አገልግሎቱን በጥራትና በተሳካ ሁኔታ እንዲያጠናቅቁ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ቢሮዉ ጠቅሷል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፤ ባለሙያዎች ፤ የሀይማኖት አባቶች እና ተጽኖ ፈጣሪዎች ሰዎች ፤ የማህበረሰብ ክፍሎች እና አጋር አካላት ለዚሁ ወሳኝ ተግባር ርብርብ እና እገዛ እንዲያደርጉም የክልሉ ጤና ጥሪ አቅርቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *