‎በበዓሉ አከባበር ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞን አመራሮችና፣የአካባቢው ተወላጆች ተገኝተዋል።

Spread the love

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው ባደሩጉት ንግግር ያደረጉት የዘንድሮውን የካፌቾ ብሔር የዘመን መለወጫ እየተከበረ የሚገኘው የንጉሱ ዘውድና ዙፋን ከ128 ዓመት በኋላ ወደ ክብሩ ሥፍራ በተመለሰበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ስሜት እንዳለው ገልፀዋል ።

‎ክልሉ በርካታ ነባር ብሔሮች ከሌሎች የሀገራችን ህዝቦች ጋር በፍቅር የሚኖሩባት በመሆኑ እንዚህ የየራሳቸው የዘመን መለወጫ በዓል ያላቸው ሆኖ በጋራና በፍቅር የሚያከብሩት መሆኑ ተናፋቂ እንዲሆን አስችሎታል ብለዋል።

‎የካፌቾ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ዘመናትን የተሻገረ እሴት መሆኑንም አንስተዋል ።

‎ከዚህ በበለጠ እንዲከበርና በዚሁ መልኩ ህዝባዊ መሠረት እንዲይዝ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎የካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምበላሽ ንጉሤ መንግስት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ እንደ ሌሎቹ ሁሉ የካፋ ህዝብ የራሱን የዘመን መለወጫ በአል ማክበርምም ባለፈ ባህሉን አዋትቶ ለሌች እንዲያሳይ እየተሰራ ቆይቶ በአሁኑ ሰዓትም ይህንን በማተናከርም የተሻለ ጃረጅ ላይ ከማድረስ እይተሰራ ነው ብለዋል።

‎አቶ ደምበላሽ አያይዘው የካፋ ንጉስ ዘውድና ዙፋን በክፍሩ ስራር እንዲመጣ ላጉደረት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎በዓሉን ሀይማኖታዊ ይዘት ጋር የሚያገናኙ አካትላ ከዚህ ድርጊት ተቆጥበው ይልቅ ለልድትው እንዲተላለፍ በጋራ መስራት ይገባል ብለልዋል።

‎የቢጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳግማዊ ማሞ የካፋ ህዝብ በራሱ የዘመን ቀመር አዝመራውን ቆጥሮ የሚያከብረው የማሽቃሮ በዓል ከምንም በላይ የተኳረፈ የሚታረቅበት ለሀገር ሰላምና ልማት ፈጣሪ የሚለመንበት ታላቅ ቀን በመሆኑ በጉጉት የምናከብረው ነው ብለዋል።

‎በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ማግስት የተካሄደ በዓላችን በመሆኑ በእጅጉ እንድናከብረው ሆኗል ብለዋል።

‎በመሆኑም የዘንድሮውን ማሽቃሮ ስናከብር ከንጉሳችን ዘውድና ዙፋን በተጨማሪ በወረዳው የባህል ማዕከል ግንባታ መሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ መሆኑ ይበልጥ ልዩ አድርጎታል ማለታቸዉን የካፋ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

‎በዓሉ የባህል ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ እየተከበረ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *